softwareteam@12
Sat, 07/12/2025 - 11:44

ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት መፍጠር ጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግስት ብሎም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት እጅግ ወሳኝ ነው " አቶ አህመድ ኑሪ
ሐምሌ 09/2017 ዓ/ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት #የፓርቲ_ተቋም_ግንባታ_ለላቀ_እምርታ በሚል መሪ ሀሳብ ለዞኑ ጠቅላላ አመራር የተጀመረው ስልጠና ሁለተኛ ቀን የስልጠናው መርሀ-ግብር በዛሬው ዕለት ቀጥሏል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ረዳት የመንግስት ተጠሪና የዞኑ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመድ ኑሪ #የብልፅግና_ፓርቲ_የአሰራርና_የአደረጃጀት_መመሪያዎች በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሰነድ
ላይ ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ወቅት እንዳሉት ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት
መፍጠር ጠንካራፓርቲ፣ ጠንካራ መንግስት ብሎም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት እጅግ
ወሳኝ ብለዋል።
ስልጠናው በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን።
መረጃው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ነው።







English

