
የኮሚሽኑ ዓላማ
በየደረጃው የኮሚሽኑን ተቋማዊ አቅም በሁለንተናዊ ረገድ በማጠናከር በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች በየወቅቱ የኢንስፔክሽን ሥራ በብቃት በማከናወን ለፓርቲው እሴት ሊጨምሩ የሚችሉ ግኝቶችን ከምክረ-ሀሳቦች ጋር ግብረ መልስ በመስጠት ለፓርቲው ጥንካሬ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ነው፡፡
ለኮሚሽኑ በተሰጡ 7 ዋና ዋና ግቦች ፣ተግባራትና ኃላፊነቶች ላይ ተገቢውን ኢንስፔክሽንና ቁጥጥር ማካሄድ፣
ግብ 1፡- የፓርቲ መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች ስራ ላይ መዋላቸውን በየሩብ ዓመቱ ክትትል ማድረግ፡፡
ግብ 2፡- የፓርቲው የፖለቲካ ጥራት መረጋገጡን በየሩብ ዓመቱ ክትትል ማድረግ፤
ግብ 3፡- በፓርቲው የሥነ-ምግባር ጤናማነት መረጋገጡን በየሩብ ዓመቱ ክትትል ማድረግ፡:
ግብ 4፡- በፓርቲ ውስጥ የፀረ-ሙስና ትግል መደረጉን በየሩብ ዓመቱ ክትትል ማድረግ፤
ግብ 5፡- የፓርቲው አካላትና አባላት መብቶች፣ ጥቅሞችና ግዴታዎች መከበራቸውን በተገቢው ሁኔታ በየሩብ ዓመቱ ክትትል ማድረግ፣
ግብ 6፡- የአባልነት መዋጮ በትክክል ተሰብስቦ ገቢ መደረጉን በየሩብ ዓመቱ ክትትል ማድረግ፤
ግብ 7፡- የአባልነት መዋጮ በትክክል ተሰብስቦ ገቢ መደረጉን በየሩብ ዓመቱ ክትትል
ግብ 8፡- የኮሚሽኑ መዋቅር እርስ በርሱና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ትብብርና አጋርነት በማጠናከር ለኮሚሽኑ ተልዕኮ ስኬታማነት አመቺ ሁኔታዎችን መፍጠር፡፡

