"ክትፎ የጉራጌ እናቶችን ጥበብን እና የማህበረሰቡን ትውፊት አጉልቶ የሚያሳይ የጉራጌ ህዝብ መለያ ምልክት ነው"
አቶ ሙስጠፋ ሀሰን
ጥር 30/2018
ዛሬ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የጉራጌ ክትፎን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናትን አስመልክቶ የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ስለፕሮግራሙ አነጋግረናቸው አጠቃላይ የፕሮግራሙን ይዘት አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተውናል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በዚህ ወቅት እንዳሉት ክትፎ የጉራጌ እናቶችን ጥበብን እና የማህበረሰቡን ትውፊት አጉልቶ የሚያሳይ የጉራጌ ህዝብ መለያ ምልክት ነው በማለት አስረድተዋል።
የክትፎ ባህላዊ አዘገጃጀትና አመጋገብ የተለየ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ወደአካባቢው እግር ጥሎት የመጣ የትኛውም እንግዳ "የጉራጌ ክትፎ በልተሃል" የሚል ጥያቄ እስከመፍጠር የቻለ መሆኑን አንስተዋል።
ጢያ ትክል ድንጋይና የጊቤ ብሄራዊ ፓርክ በሁለቱም ዞኖች በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ የቱሪስት ስፍራዎች መሆኑን ያወሱት ዋና አስተዳዳሪው አቶ ሙስጠፋ በጉራጌ ሁለቱም ዞኖች አካባቢ በርካታ ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርሶችና የተፈጥሮ ፀጋዎች ባለቤት በመሆኑ በቅርስነት ለማስመዝገብ በየደረጃው ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል።
ክትፎን በአለም ቅርስነት የጉራጌ መለያ ምልክት ሆኖ እንዲመዘገብ የሁለቱም የጉራጌ መዋቅሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።










ይከታተሉ 👇👇follow ያድርጉ!
በዌብሳይታችን https://www.misraqguragezoneprosperityparty.org.et/
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61572637620777
በቴሌግራም
https://t.me/eastguragezoneprosperityinfo
በቲክቶክ
www.tiktok.com/@mesraqguragezonep
የጉራጌ ክትፎን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናት ላይ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ጥር 30/2018
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረ/ፕ አበባው አያሌው በተገኙበት የጉራጌ ክትፎን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናት ላይ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያለው ተወዳጅና ተመራጭ የሆነው የክትፎ ምግብ ዓለም አቀፍ ቅርስ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረ/ፕ አበባው አያሌው፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ ፤ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ጨምሮ የክልል አመራሮች፣ የሁለቱም ዞን አፈ ጉባኤዎች፤ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊዎች፤ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል፣ የጉልባማ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ለዘወትር ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ከታች ያሉ ገፃቻችንን ይከታተሉ 👇👇follow ያድርጉ!
በዌብሳይታችን https://www.misraqguragezoneprosperityparty.org.et/
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61572637620777
በቴሌግራም
https://t.me/eastguragezoneprosperityinfo
በቲክቶክ
www.tiktok.com/@mesraqguragezonep















"የህዝቡን አንድነት በማጠናከርና የተናጠል አቅሞችን በማስተባበር የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት በቅንጅት እየተሰራ ነው"
አቶ ሙስጠፋ ሀሰን
#ቡታጅራ| ጥር 28/2018
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ከመንግስት፣ ከማህበረሰቡና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በምስራቅ ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ በአጠቃላይ ከ140 በላይ ፕሮጀክቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ በመተግበር ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ መካከል በዋናነት ዛሬ የተመረቁት የዳሙ ጤና ጣቢያ፣ የጎጌቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና የኬላ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ይገኝበታል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስጠፋ ሀሰን በዛሬው ዕለት ፕሮጀክቶቹን መርቀው በከፈቱ ጊዜ እንዳሉት የህዝቡን አንድነት በማጠናከርና የተናጠል አቅሞችን በማስተባበር የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ለዚህም ማሳያ የሚሆነው የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ከመንግስት፣ ከማህበረሰቡና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በከተማና በገጠር የህዝቡን አንድነት በማጠናከርና የተናጠል የህዝብ አቅሞችን በማሰባሰብ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እየቀረፈ ይገኛል ብለዋል።
ማህበሩ በትምህርት፣ በጤናና የኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ላይ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው አቶ ሙስጠፋ በዛሬው ዕለት የተመረቁት ፕሮጀክቶች ለሌሎች አካባቢዎችም አርአያ የሚሆን ለሌላ የልማት ስራዎች መነቃቃትን የፈጠሩ የህዝቡን የረጅም ግዜ ችግር የቀረፉ ናቸው ብለዋል።
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር በመንግስት ሊሸፈኑ የማይችሉ የልማት ክፍተቶችን በመሙላት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራቱን የገለፁት አቶ ሙስጠፋ ለእነዚህ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ድጋፍ ላደረገው 'የግሊመር ኦፍ ሆፕ' ግብረ ሰናይ ድርጅት ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም የልማት ስራዎች ህዝቡ ለጉልባማ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልና የተመረቁ ፕሮጀክቶችን ባለቤት ሆኖ በመጠበቅ ዘላቂ በሆነ መንገድ እንዲጠቀምባቸው የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የልማትና ባህል ማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቅባቱ ተሰማ በበኩላቸው በዛሬው እለት የተመረቁት የደቡብ ሶዶ ወረዳ የተቀናጁ የልማት ስራዎች በልማትና ባህል ማህበሩ አባላት፣ 'ግሊመር ኦፍ ሆፕ' በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅትና በአካባቢው ማህበረሰብ ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ ትብብር የተገነቡ ናቸው ብለዋል።
ለእነዚህ 80 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ከ284 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ወጪ መሆኑን የገለጹት አቶ ቅባቱ የልማት ስራዎቹ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ፣ በየአካባቢው የነበሩ ችግሮችን የሚፈቱና የልማት ክፍተቶችን የሚሞሉ ናቸው ሲሉም አክለዋል።
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አድማሱ የልማትና ባህል ማህበሩ በወረዳው በልዩ ልዩ የልማት መስኮች ላይ በስፋት በመሳተፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል። እነዚህ ድጋፎች የአርሶ አደሩን ኑሮ በማሻሻል በኩል ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል ።
የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የልማትና ባህል ማህበሩ በጤና፣ በትምህርትና ሌሎች የልማት ስራዎች ድጋፍ በማድረግ ለማህበረሰቡ ህይወት መለወጥ ከፍተኛ ሚና በመወጣት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በፕሮግራሙ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣ የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቅባቱ ተሰማ፣ የግሊመር ኦፍ ሆፕ የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ለዘወትር ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ከታች ያሉ ገፃቻችንን ይከታተሉ 👇👇follow ያድርጉ!
በዌብሳይታችን https://www.misraqguragezoneprosperityparty.org.et/
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61572637620777
በቴሌግራም
https://t.me/eastguragezoneprosperityinfo
በቲክቶክ
www.tiktok.com/@mesraqguragezonep




















ሀገራዊ 7ኛ ዙር ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ እንዲሆን የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል፤
ጥር 27/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከክልል ወጣት አደረጃቶች በክልሉ በሚገኙ ስብዕና ማእከላት ፤ በበጎ ፈቃድ አፈጻጸም እና በ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍታዊና ታአማኒ እንድሆን የወጣቶት አደረጃጀቶች የሚኖራቸዉ ሚና ለማጠናከር የምያግዝ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ በመድረኩ የወጣት አደረጃጀቶች በየደረጃው ምን እየሰሩ እንደሆነና ከህብረተሰብ ጋርም ያላቸው ቁርኝት ምን እንደሚመስል ማየት የተቻለበት መሆኑን ተናግረዋል።
በሁሉም ዘርፍ የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማወቅ እንደ ክልልም ሆነ እንደ ሀገር የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣት በቅንጅት እየተሰራ ያለ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክረምትና የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በየመስኩ እየተከናወነ ይገኛል ያሉት ኃላፊው በሁሉም አካባቢዎች በተሰራው በርካታ ስራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል። በተመሳሳይ ከመንግስት የሚወጣ በርካታ ወጪዎችን ማዳን ስለመቻሉም አክለዋል።
በዚህም በመዋቅሮች መካከል የሚታዩ ልዩነቶች ወደ ተመሳሳይ ለማምጣት መዋቅሮች ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ያሉት ኃላፊው ትኩረት በሰጡ መዋቅሮች የመጣው ለውጥ ምስክር ነው ብለዋል።ቢሮው የህዝብን ተጠቃሚነት አስቀድመው ለሚሰሩ እውቅና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
የበጎ አድራጎት ስራ በማህበረሰቡ ውስጥ ባህል እየሆነ ስለመጣ በየደረጃው ያለ አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ ስራዎችን እያስገመገመና እየገመገመ የሚሰራውን ስራ ሊያጠናክር እንደሚገባም ገልጸዋል።
በየደረጃው ያሉ የወጣቶች ማዕከላት ሊደገፉ ይገባል ያሉት አቶ ጌታቸው ማዕከላትን ከማደራጀት አንጻር እንደ ቢሮ በርካታ ስራዎች መሰራቱን ተናግረዋል።ሁሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ እንተሚሰራም አስታውቀዋል።
በቢሮው ደረጃ የወጣት ማዕከላት ላይ ልዩ ዕቅድ ታቅዶ እንደሚሰራ ያስታወቁት አቶ ጌታቸው አደረጃጀቶችም ድርሻቸው እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ የወጣቶች አደረጃጀቶች በቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮ የሆነውን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ እንዲሆን የወጣቶች፣ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ በመገንዘብ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
አቶ ጌታቸው ያሉን አቅሞችን በማጠናከር የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ስራ ለመስራት በዛሬ መድረክ አንዱ ከሌላው ተሞክሮውን ለመቅሰም ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማጠናከር ያስቻለ ነው ብለዋል።
የቢሮው ምክትልና የወጣት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊ በመድረኩ የተነሱ ሀሳቦችን ግብዓት በማድረግ ለወጣቱና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በትኩረት ለመስራት ታቅዶበት ተግባራዊ እርምጃዎች ይሰራል ብለዋል።
የወጣቶች አደረጃጀት በየአካባቢያቸው ያሉ የወጣቶች ማበልጸጊያ ማዕከላትን በቅርብ ክትትል እንዲደግፉም አሳስበዋል።









ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፣
▶ ክልሉን በአዲስ መልክ ስናቋቁም አጠቃላይ የመልማት አቅምና የጠቅላላ እድገት (GDP) በማጥናትና የእቅድ አካል በማድረግ በተቀናጀ መንገድ ወደ ስራ ገብተናል።
▶ በእቅድ ዝግጅት ላይ ለየት ያለ አካሄድን በመከተል በእቅዱ ላይ ሰፋ ያለ ውይይትና ተከታታይ ምዘና እንዲካሄድ ተደርጓል።
▶ በዚሁ ጥናት መሰረት ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ በጠባብ መሬቶች ላይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ልዩ ትኩረት ተደርጓል።
▶ በግምገማችን መሰረት ጤናማ አካሄድ ላይ መሆናችንን አይተናል።
▶ የህዝብ እርካታ ተረጋገጠ የሚባለው የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ ነው። ብዙ የልማት ጉድለቶችና ክፍተቶች አሉ። በመሆኑም አመራሩ መዘናጋት የለበትም።
▶ በክልሉ በሰላም ረገድ በተሰሩ ስራዎች ያልተገደቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች አሉ።
▶ በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ ነባር ችግሮችን ለመፍታት ጊዜ፣ ጥንቃቄና የአመራር ጥበብንና ምቹ ሁኔታዎችን ይፈልጋሉ።
▶ ለእነዚህ አካባቢዎች ችግር መፈታት ምክር ቤቱ አበክሮ ሊሰራ ይገባል።
▶ የውዥንብርና ግጭት አጀንዳዎችን ማስተካከልና ትክክል አይደለም የማለት ሃላፊነት አለበት።
▶ የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል ምርታማነትን ማሳደግና ምርትን ወደ ገበያ ማውጣት ይገባል።
▶ እንደ ክልሉ በአሁኑ ወቅት የአርሶ አደሩ ምርት ቀጥታ የሚቀርብባቸው 158 የሰንበት ገበያዎች አሉ።
▶ የገበያ ትስስርን፣ ኢኮኖሚያዊ ልውውጥን ማጠናከር የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል ትልቅ ድርሻ አለው።
▶ በህገ ወጥ የነዳጅ ዝውውርና ሽያጭ ላይ ህጋዊ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው።
▶ በሚጓተቱ የውሃ፣ የመንገድ ግንባታና ሌሎች የክልልና የፌደራል ፕሮጀክቶች ላይ ክትትልና ግምገማ እየተካሄደ ነው።
▶ እንደ መንገድ ያሉ ፕሮጀክቶች በመንግስት ብቻ አይሰሩም፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን ማጠናከር፣መተጋገዝ ይገባል።
▶ በዚህ ረገድ በክልሉ የሚታየው የህብረተሰብ ተሳትፎ የሚያኮራ ነው፣ ለክልሉ ሁለንተናዊ ስኬትም ትልቅ ድርሻ ነበረው።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ።
#ቡታጅራ| ጥር 22/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ንግድ ፅ/ቤቶችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት በቡታጅራ ከተማ አካሄደ።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ቤተልሔም ታደሰ የሴክተሩ ዋና ዓላማ ፍትሀዊ የንግድ አሰራርና ዘመናዊ የግብይት ስርዓትን በመዘርጋት መልካም አስተዳደርን በማስፈን የንግዱ ማህበረሰብና የሸማቹን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ይበልጥ በማረጋገጥ የዕርካታ ደረጃቸውን ማሳደግ እንደሆነ በመድረኩ ገልፀዋል።
ኃላፊዋ ወ/ሮ ቤተልሄም አክለውም እንዳሉት መምሪያው የተጣለበትን ሀላፊነት ለመወጣት ባለፈው ዓመት የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸው በያዝነው በጀት ዓመትም በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ተግባራቱም እየተገመገሙ የመጡበት አግባብ እንዳለ አንስተዋል።
በበጀት ዓመቱ ችግር ፈቺ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በቀጣይም የንግዱ ማህበረሰብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ተከታትሎ ለመፍታት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከንግድ ፍቃድ ዕድሳትና የመጠቀሚያ ጊዜ ካለፈባቸው ምርቶች ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ቢሰራም የሚጠበቀውን ለውጥ ማምጣት ስላልተቻለ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ኃላፊዋ ወይዘሮ ቤተልሔም አሳስበዋል።
የሰንበት ገበያ የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍ በየአካባቢው የተቋቋመ ቢሆንም ከዋጋ ንረት አንጻር የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በአካባቢው የሚመረቱ እንዲሁም የፋብሪካ ምርቶችን በትስስር አቅርቦትን ለማሳደግ የተጀማመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።
ከህገ ወጥ የነዳጅ ስርጭት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ጉድለቶችንም በመለየት በየደረጃው ያሉ ግብረ ሀይሎችን በማሳተፍ የቁጥጥር ስራ በተጠናከረ ሁኔታ መሰራት ያለበት መሆኑን አመላክተዋል።
ነጋዴው እንዲሸጥበት የተለጠፈውና የሚሸጥበት ዋጋ ክትትልና ቁጥጥር መደረግ ያለበት ስለሆነ በሰንበት ገበያ ውስጥ ያሉ ነጋዴዎችም በገቡት ውል መሰረት የማይሰሩ ከሆነ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከገበያ የሚወጡበት አግባብ ስላለ ሸማቹ ማህበረሰብም ጥቆማ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ የተቋሙ የማኔጅመንት አካላት አስተያየት ሰጥተዋል።
በግምገማው የተገኙ አካላትም ተቋሙ ወርዶ የሚሰራቸውን የድጋፍና ክትትል ስራዎችን አድንቀው በሚቀጥሉትጊዜያትም ተጋግዘን ከሄድን ውጤታማ ስራዎችን የምንሰራበት ዕድል ይፈጠራል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በውይይቱም ወቅትከግማሽ ዓመቱ ሪፓርት በተጨማሪ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ እና የንግድ አደረጃጀቶች የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩም የከተማና የወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የከተማና የሶስቱም ቀበሌ አመራሮች፣ የከተማና ወረዳ የተቋሙ የልማት ዕቅድ ባለሙያዎች፣ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አመራሮች፣ የነጋዴ ሴቶች ማህበራት አመራሮች፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ ሸማች ማህበራት እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።


















የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ህንፃ ዲዛይን ቀርቦ በካቢኔ ተገመገመ
#ቡታጅራ| ጥር 18/2018 ዓ/ም
በዛሬው ዕለት የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ቢሮ ችግር የሚፈታ ህንፃ ዲዛይን ቀርቦ በካቢኔ የተገመገመ ሲሆን የህንፃው ዲዛይን በዘርፉ ከፍተኛ የስራ ልምድ ባለው ኤች ኤች አማካሪ አርክቴክትና ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በድርጅቱ ከፍተኛ አርክቴክቶች ስለህንፃው ዲዛይን የውስጥና የውጭ የህንፃው ይዘት በዝርዝር ለካቢኔው አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ዲዛይኑን ሰርቶ ያቀረበው ኤች ኤች አማካሪ አርክቴክትና ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጨበራ ጩርጩራ፣ ጎርጎራን የመሳሰሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እንዲሁም የጥያን እና የቡታጅራን የጫካ ፕሮጀክት ዲዛይን ሰርቶ ያቀረበ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያለው ድርጅት መሆኑን አስታውሰው ለዞኑ አስተዳደር ህንፃ የቀረበው ዲዛይንም የዞናችንን ማህበረሰብ የሚመጥን፣ ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የ"መሶብ/mesob/ አገልግሎትን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ፣ ለቡታጅራ ከተማም ከፍተኛ ውበትን የሚጨምር የአስተዳደር ህንፃ ዲዛይን መቅረቡን ገልፀዋል።
የዞኑ የካቢኔ አባላትም የቀረበው የአስተዳደር ህንፃ ዲዛይን ዘመናዊ የሆነና በአንድ ማዕከል ለዞናችን ተገልጋዮች አገልግሎት ለመስጠት እጅግ ምቹ የሆነ፣ ከቢሮዎች ባሻገር የአዳራሽ፣ የካፌና ሌሎች የህፃናት ማቆያን ጨምሮ ሰብዐዊ አገልግሎት እንዲኖረው ታስቦ መዘጋጀቱ በጣም ተገቢና ዘመኑን የዋጀ መሆኑን አስተያየት የሰጡ ሲሆን ነገር ግን ከህንፃው ፊትለፊት የጉራጌን ባህላዊ ቤትና እሴቶቹን የሚገልፅ መግቢያ ላይ ቢኖረው የሚል አስተያየት ሰጥተወ፤ ይህ ህንፃ እንዲገነባ እንደአመራር መላው ማህበረሰብን በማስተባበር ባጠረ ግዜ ለመጨረስ መረባረብ ይኖርብናል የሚሉ አስተያየቶች ሰጥተዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ይህ የህንፃ ዲዛይን ከውስጥ ባህላዊ መገለጫዎች ያሉት ቢሆንም በተሰጠው አስተያየት መሰረት የህንፃው መግቢያ ላይ ባህላዊ መገለጫዎች እንዲኖሩት ማስተካከያ እንዲኖረው ይደረግ በሚል ለባለሙያዎቹ የገለፁ ሲሆን ይህ ህንፃ በ3 ዓመት አጠናቀን ለአገልግሎት ብቁ ማድረግ ታቅዷልና በቅርቡ በተዘጋጀው ቦታ ላይ የመሰረተ ድንጋይ በማኖር ግንባታው እንደሚጀመር አሳውቀዋል።
በመጨረሻም ዲዛይኑን ሰርቶ ላቀረበው ኤች ኤች አማካሪ አርክቴክትና ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዘመናዊ የአስተዳደር ህንፃ ዲዛይን ሰርቶ በማቅረቡ ከፍተኛ ምስጋናቸውን በራሳቸው፣ በዞኑ መንግስትና ህዝብ ስም ያቀረቡ ሲሆን ድርጅቱ የተሰጠውን ማስተካከያና ቀሪ ቴክኒካል ስራዎች በአጭር ግዜ ሰርቶ እንዲያቀርብ አሳስበዋል።
በመድረኩ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አመራርና ባለሙያዎች እና ኤች ኤች አማካሪ አርክቴክትና ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባለሙያዎች ተገኝተዋል በማለት የዘገበው የምስራቅ ጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።















"በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የአሰራር ስርዓትን ማዘመን ተገቢ ነው " ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር )
(ጥር 16/2018)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ማስጀመሪያ ፕሮግራም በሆሳዕና ከተማ ተካሒዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የአሰራር ስርዓትን ማዘመን ተገቢ ነው ብለዋል።
ሀገራዊ የሪፎርም ኦሳቤን ውጤታማ ለማድረግ የአመራር ጥበብን ተጠቅሞ መፍትሄ መፈለግ ይገባል ብለዋል።
ባለፉት ዓመታት ያጋገሙንን ችግሮች በመሻገር አሁን ላለንበት ደረጃ በቅተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አመራሩ የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለመፈጸም ያለው ዝግጁነት ውጤታማ ስለመሆኑም አስረድተዋል።
ከአመራሩ ባለፈ በፈጻሚዎች ዘንድ ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት የተሻለ እንዲሆን ያለው ተነሳሽነት እየጨመረ መምጣቱን አብራርተዋል።
ሪፎርሙን ለማሳካት አመራሩ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ተጨባጭ እቅድ ማዘጋጀት እና በቂ ተግባቦት መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በቂ አደረጃጀት እና አሰራር ፈጥሮ ወደ ተግባር ከመግባት ባለፈ ፣ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ፣ እውቀትን ሀብትን እና ገንዘብን አቀናጅቶ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ውጤት የሚያመጣና ለተሻለ ለውጥ የሚያነሳሳ የድጋፍና ክትትል ስራ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በሪፎርሙ ውጤት ማምጣት ላይ ማተኮር እንዲሁም
በችግር የተተነተኑ ጉዳዮችን መቀልበስ ይገባል ብለዋል።
የህብረተሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ውጤት ማስመዝገብ ተገቢ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በስራ መመሪያቸው አመላክተዋል።
የኢፌዲሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደ ሀገር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ጠንካራ እና ዘመን ተሻጋሪ ተቋም መፍጠር ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፈተሽ የጋራ ተግባቦት መፍጠር እንደሚገባም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙ በመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲ ውስጥ ዲዛይን ሲደረግ ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።
ፖሊሲው ከሀገር አቀፍ ባለፈ የአለምን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ከመንግስታዊ አገልግሎት አንጻር ኢትዮጵያ ያለፈችባቸው ጉዞዎች ውጤታማ እንዳልነበር አስታውሰዋል።
እንደ ሀገር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የስራ ባህልን በማሻሻል መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።
ተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ የሁሉንም አካላት የጋራ ጥረት ይጠይቃል ሲሉም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።
ሪፎርሙ ሁሉ አቀፍ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ትራንስፎርም በማድረግ ተቋም መገንባት ላይ በትኩረት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
ፖሊሲው በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ለውጥ ማምጣትን ታላሚ ያደረገ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ
ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት አቅርቦት ስርዓት መዘርጋት አብይ ጉዳይ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ጠቅሰዋል።













"የአፈር ለምነቱ እንዲጨምር ብሎም የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል ቀጣይነት ያለው የተቀናጀ የተፋሰስ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል" አቶ ሙስጠፋ ሀሰን
#ቡታጅራ| ጥር 16/2018
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ዳሙ 03 ቀበሌ በመገኘት የ2018 ዓ/ም ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራን በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።
የተፋሰስ ልማት ሥራን የዞኑ ማህበረሰብ ባህል እያደረገው መምጣቱን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው እንደ ዞን በ16,275 ሄክታር መሬት ላይ የታቀደው የስነ-አካላዊና የስነ ህይወታዊ ሥራ እንዲሳካ ሁሉም ሰው ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባና እንደ ዳሙ ያሉ መልከዐ-ምድራቸው ወጣ ገባ የሆኑ አካባቢዎች የአፈር መሸርሸርና ድርቅን ለመቋቋም ቀጣይነት ያለው የተፋሰስ ልማት ሥራ በመስራት ተፈጥሮን መጠበቅ እንደሚያሰፈልግ አስረድተዋል።
ከዚህ በፊት በተሠሩት የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራ ትልቅ ጥቅም እንዳስገኘ ለአብነትም የአፈር ለምነት፣ የከርሰ ምድር ውሃና የምርት መጠን እንዲጨምር ማድረጉን በመጥቀስ እንደ ሀገርም ትልቅ ስኬት ማስመዝገብ የተቻለበት በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል።
በዞን ደረጃ የተያዘው የ16ሺ 275 ሄክታር የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ዕቅድ በ25 ቀናት ለማሳካት በሁሉም በዞኑ ሥር ባሉ ቀበሌዎች ሌት ተቀን በመከወን እንዲረባረቡ ዋና አስተዳዳሪው አቶ ሙስጠፋ ጥሪ አቅርበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ም/አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሱ አበጋዝ በዛሬው የ2018 ዓ/ም ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ይፋዊ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት መንግስት ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የተፈጥሮ ሥነ-አካላዊና ስነ ህይወታዊ፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎች በትኩረት በመስራቱ የአፈር መከላትና የለምነት መጠን እንዲጨምር አስችሏል ብለዋል።
ይህም የተፈጥሮ ሚዛን እንዲስተካከል በማድረግ ተጎድቶ የነበረን አፈር እንዲያገግም በማድረግ በግብርናው ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አዎንታዊ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልፀዋል።
የ2018 ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ተግባር ከዚህ በፊት ያሉን ተፈጥሮን የመንከባከብ ልምድ በመጠቀም በ92ቱም የንዑስ ተፋሰሶች 16ሺ 275 ሄክታር ላይ የታቀዱት የስነ-አካላዊና ሥነ-ህይወታዊ ተግባራት 149,868 የህብረተሠብ ክፍሎችን በማሳተፍ ለማሳካት በዛሬው እለት በይፋ መጀመሩን ገልፀዋል።
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አድማሱ በበኩላቸው በዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ በወረዳችን በምትገኘው ፍፁም ሠላማዊና የጥንታዊ ባህልና ቅርስ ባለቤት በሆነው ዳሙ 03 ቀበሌ ይፋ በመደረጉ የተሠማቸው ደስታ ገልፀዋል።
እንደ ወረዳ በ2018 ዓ/ም በ17 ንኡስ ተፋሰስ 3ሺ 255 ሄክታር መሬት የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራ እንደሚሠራ የገለፁት የደቡብ ሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን 19,541 የህብረተሠብ ክፍሎች እንደሚሳተፉበት አስታውቀዋል።
ሠው ሠራሽ ሠደድ እሳትና የከሰል ምርት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ህዝቡ ሊከላከል ተፈጥሮን ሊጠብቁና ሊንከባከቡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ዘገባው፦ የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።













የጥቁር አንበሳው ክንፍ በሰማዩ ላይ ነግሦ አምሽቷል - የ90 ዓመታት የክብር ጉዞ! 🔥
**************************
የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ምሽት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እጅግ ዘመናዊ እና አስደናቂ የድሮን ትርዒት ቀርቧል።
በልዩ ትርዒቱ የተሳተፉት በሺዎች የሚቆጠሩ ድሮኖች በቢሾፍቱ የኢትዮጵያን ሰማይ በተለያዩ መልዕክት አዘል ቀለሞች እና ቅርጾች ሲያደምቁት አምሽተዋል።
በዚህም የአየር ኃይሉ የ90 ዓመታት የጀግንነት ጉዞ እና የዘመናዊነት ሽግግር በብርሃን ትርዒት ለዓለም ታይቷል።
ታዳሚዎችን በእጅጉ ያስደመመው ትርዒት የአየር ኃይላችንን የጥንካሬ እና የኩራት ተምሳሌትነት ዳግም አረጋግጧል።
ሁነቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ራሱን በዘመናዊ ትጥቅ እና በሰው አልባ አውሮፕላኖች በማደርጀት የአፍሪካ የኩራት ተምሳሌት መሆኑን ለዓለም ያረጋገጠበት አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።
ተጨማሪ የኢቢሲ ዶትስትሪም የዲጂታል አማራጭ አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያግኙ፡-
#EBCDotstream #Ethiopia #AirForce #90thanniversary #airshow #Africa










የምስራቅ ጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በባለፉት 6 ወራት ከ1 ቢሊዮን 215 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ ።
#ቡታጅራ| ጥር 15/2018 ዓ.ም
በምስራቅ ጉራጌ ዞን በተያዘዉ በጀት ዓመት በ6/ስድስት/ ወራት ከመደበኛ እና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከ1 ቢሊዮን 215 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የምስራቅ ጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ይሽልጌታ በላይነህ ገልጸዋል።
የ2018 የመጀመሪያው ግማሽ በጀት አመት የገቢ አፈጻጸም በመምሪያው ማኔጅመንት አባላት እና አጠቃላይ ባለሙያዎች በተገኙበት መገምገሙን የገለፁት ኃላፊው እንደ መምሪያ በስድስት ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ከተያዘዉ እቅድ አንፃር 108% ገቢ መሰብሰቡ እንደተገመገመ ገልፀዋል፡፡
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ይሽልጌታ አክለውም እንዳሉት ገቢዉ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 498,432,754 (40.99%) ብር ብልጫ ያለው መሆኑ ጠቁመዋል፡፡
በዞኑ በአዲሱ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 የክህሎት ስልጠና በመስጠት፣ የግብር ከፋዮችን የገቢ መሰረት በማስፋት፣ ደረጃ ሽግግር የማሻሻል እና የታክስ ህግ የማስከበርና መልካም አስተዳደርን ማስፈን ላይ ውጤታማ ስራዎች እንደተሰሩ ተናግረዋል፡፡
በግማሽ አመቱ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ለቀጣይ በላቀ ትጋት በመፈፀም በቀሪ ስድስት ወራት ከ1ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱንና ባለሙያው ከመደበኛ የስራ ሰዓት በተጨማሪ ሙሉ ጊዜውንና አቅሙን ተጠቅሞ መስራት እንዳለበት እንዲሁም ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡን ገልፀዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ በትምህርት ቤት ድጎማ በጀት አተገባበርና በተማሪዎች ውጤት ማሻሻል ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ
ጥር 15/2018 (ቡታጅራ)
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ በትምህርት ቤት ድጎማ በጀት አተገባበርና በተማሪ ውጤት ማሻሻል ልዩ ዕቅድ ላይ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሰልማን ሳኒ እንደተናገሩት የውይይቱ ዋና ዓላማ የትምህርት ቤት የድጎማ በጀት አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ልዩ ዕቅድ የታቀደ ሲሆን ዕቅዱን እስከ ትምህርት ቤት በማውረድ በዲሲፕሊን እንዲመራ መግባባት ላይ ለመድረስ ታልሞ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አቶ ሰልማን አክለውም በዚህ ዓመት የትምህርቱን ስራ በተሻለ መልኩ ለመምራት ና የተማሪዎች ውጤት ከነበረበት ስብራት ወጥቶ የተሻለ አፈጻጸም ላይ ለመድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።
አያይዘውም ከሁለተኛ ሴሚስተር ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ የቲቶሪያል ትምህርት የሚሰጥ ሲሆን አሰጣጡም በትምህርት ቤት ደረጃ ተዘጋጅቶ በተመረጡ መምህራን የሚሰጥበት ሁኔታ እንደሚኖር አስገንዝበዋል።
ከድጎማ በጀት ጋር ተያይዞ ትምህርት ቤቶች ከኢኒሼቲቭ ሰራዎች ጋር በማስተሳሰር ጥንቃቄ ባለውና መመሪያና ደንብን ተከትለው መስራት እንዳለባቸው አንስተው ከኢኒሼቲቭ ስራዎች ውስጥም ሲፒዲ እና ሌሎች የመምህራን አቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ላይ መጠቀም እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ ልማት ዕቅድ ባለሙያ አቶ እንዳሻው ማሰሬ የድጎማ በጀት አጠቃቀም አስመልክቶ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የተማሪዎች ሰታቲክሳዊ መረጃዎች በአግባቡ ተደራጅተው ሊቀመጡ እንደሚገባ ገልጸው በቀጣይም እየተረዳዳንና እየተጋገዝን እንሄዳለን ብለዋል።
የድጎማ በጀቱ ሀምሳ ፐርሰንት ትምህርት ቤቱን ሊያግዝ የመጣ ስለሆነ አሰራሩንና መመሪያውን ጠብቆ መተግበር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በውይይቱ ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቶባቸው የእለቱ መድረክ ተጠናቋል።
በመድረኩም የወረዳና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት አመራሮችና የልማት ዕቅድ ባለሙያዎች እንዲሁም የመምሪያው የማኔጅመንት አካላት ተገኝተዋል።





ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተሰናዳው የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 ይፋዊ የመክፈቻ መርሃግብር ላይ ተገኝተዋል።
ኤክስፖው “የወደፊቱን የአቬሽን አቅም በጋራ እንገባ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን ኢትዮጵያ ለአቪዬሽን እና ኤሮስፔስ ልማት፣ አለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር እና ሀገራችንን በአቪዬሽን ልማት የቀጣናው እና አኅጉሩ የፈጠራ፣ የክህሎት ልማት እና የዘላቂ እድገት ማዕከል ማድረግ ላይ ያላትን ጽኑ አቋም እና ተግባር ያሳያል።
#Prosperity










"ወጣቶች የሰላም አምባሳደር በመሆን ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለማጠናከር የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል" አቶ ታዬ ተስፋዬ
#ቡታጅራ | ጥር 15/2018 ዓ.ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታዬ ተስፋዬ ወጣቶች የሰላም አምባሳደር በመሆን ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ይበልጥ ለማጠናከር የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በዞኑ 3ኛው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርቶች ውድድር እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ መካሄድ ከጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።
በትናንትናው ዕለት በመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ከሰባቱም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የመጡ የሰላም አምባሳደር ወጣቶች የዞኑ ህዝቦች ትስስር የሚያጠናክር ስጦታ ተለዋውጠዋል።
በዚህ ወቅት መምሪያ ኃላፊው አቶ ታዬ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ድርሻ እንዳለቸው ገልፀው በዚህ ውድድር ለመካፈል የመጡ ወጣቶች ያሳዩን አንደኛው ለሌላኛው መዋቅር ስጦታ የመለዋወጥና ፍፁም የወዳጅነትና አብሮነት ማሳያ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀው ለወጣቶቹ በመምሪያውና በስፓርቱ ቤተሰብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።።
ኃላፊው አቶ ታዬ አክለውም እንዳሉት በውድድሩ ጅማሮ የታየው ስፖርታዊ ጨዋነት እስከ ፍፃሜው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።













" የአርሶአደሩን የፋይናንስ አካታችነት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት እውን ማድረግ የግብርናው ዘርፍ ማዘመንና ሁለንተናዊ የቤተሰብ ብልፅግናን ማረጋገጥ ነው" አቶ መሰለ ጫካ !!
#ቡታጅራ | ጥር 14/2018
" የተቀናጀ የግብርና ልማት ጥረት ለቤተሰብ ብልፅግና ስኬት!" በሚል መሪ ቃል የምስራቅ ጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የበልግ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠለ ጫካ" የአርሶአደሩን የፋይናንስ አካታችነት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት እውን ማድረግ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመንና ሁለንተናዊ የቤተሰብ ብልፅግናን ማረጋገጥ መሆኑን ገለፀዋል።
አቶ መሠለ አክለውም "በመፍጠርና በመፍጠን አንዱን ተግባር በብዙ እጥፍ በመተግበር ግብርናችንን ማሳለጥ ይገባናል" ያሉ ሲሆን፤ አርሶ አደሮቻችን የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ተጠቃሚ በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
አያይዘውም ሁሉም የግብርና ዋና ዋና ስራዎቻችን በንቅናቄ ታግዘው እንዲከናወኑ በማድረግ ምርትና ምርታማነታችን ማረጋገጥ ከሁሉም የዞኑ ህዝብ ይጠበቃልም ብለዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሱ አበጋዝ በበኩላቸው የ2018 በጀት አመት የበልግ ወቅት የተቀናጀ ግብርና ልማት ንቅናቄ ሲካሄድ በተቋሙ የተያዙ ዋና ዋና የተፋሰስ ልማት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የበልግ ሰብል ምርት፣ የቡናና ቅመማ ቅመም፣የሜካናይዜሽን ሽግግር፣ የሌማት ትሩፋት፣ የፋይዳ መታወቂያ፣ የተቀናጀ የቤተሰብ ብልፅግና፣ የፋይናንስ አካታችነት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት እና ሌሎቹም ግቦች በውጤታማነት በማከናወን የቀጣይ ተግባራት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ተግባር ለመግባት ነውም ብለዋል።
አያይዘውም በበጀት አመቱ የተቀናጀ አመራር፣ የባለሙያ ትጋትና ቁርጠኝነት፣ የተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ እና የቴክኖሎጂ ስርጭት ስርዓት በማዘመናችን በግብርናው በሁሉም ዘርፎች ምርትና ምርታማነታችን ላቅ ያለ አፈፃፀም እንዲኖረው በማድረግ ስድስቱ የግብርና ምሰሶዎችን ማሳካት ችለናል ሲሉም ተናግረዋል።
አክለውም የአርሶአደሮቻችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና የፋይናንስ አካታችነት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት በርካታ ተግባራት አከናውነናል ያሉ ሲሆን፤ የብድርና የዋስትና አማራጮች ተዘጋጅቶላቸው አርሶአደሮቻችን የግብርና ሜካናይዜሽን በመጠቀም የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱም ከንግድ ባንክ ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
የቡታጅራ ከተማ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ወርቁ በመድረኩ በመገኘት " የአርሶ አደሮች ቤተሰብ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት አርሶ አደሩ የስራ ማስኬጃ ብድር፣ የፕሮጀክት ፋይናንስ ብድር፣ የግብርና ማሽነሪዎች እና ሌሎችም ብድሮች መዘጋጀታቸውን በመግለፅ፤ አርሶ አደሩ ወይም ለህብረት ስራ ማህበራት በቀጥታ የተዘጋጀ ብድር መሆኑንም አስረድተዋል።
በዚህም ተበዳሪው ከመበደሩ በፊት የንግድ ባንክ ደምበኝነቱ ከ3 ወር እስከ 6 ወር ቀድሞ ተጠቃሚ በመሆን በመመሪያና በአሰራሩ መሰረት የሚያገኘው ይሆናልም ተብሎዋል።
ተሳታፊዎች ላነሷቸው ሃሳብ አስተያየቶች ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸው የዕለቱ መድረክ ተጠቃሏል በማለት የዘገበው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።


















የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ማስከበር ስራዎች ዙሪያ ከአጎራባች ክልል የዘርፉ ኃላፊዎችና ከሀገር መከላከያ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በጢያ ከተማ ውይይት አካሄደ።
ጥር 14/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ያሉ ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች በምስራቅ ጉራጌ ዞን በአለም ዓቀፍ የቅርስ መገኛ ጢያ ከተማ ተገምግሟል።
በማዕከላዊ ኢ/ያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በሚገኘው ሶዶ ወረዳ እና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሚገኙት ሶዶ ዳጪ፣ ቀርሳ ማሊማ ፣ ሰዴን ሶዶ ወረዳዎች፣ አዋሳኝ አካባቢ ያሉ የፀጥታ ሁኔታ በጋራ ጥምር ግብረ-ሀይል ተገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ቢሮው በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ማስከበር አቅጣጫዎች ዙሪያ ከሰላምና ጸጥታ መዋቅር ሃላፊዎችና ከፖሊስ ከሀገር መከላከያ የጦር መኮንኖች ጋር ውይይት አካሄዷል ።
የቢሮው ሃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳና በአጎራባች ኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የጸጥታ ችግሮችንና የግጭት አዝማሚያዎችን በአጭር ጊዜ በጋራ በልዩ ሁኔታ ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በክልሎቹ እንደ ሀገር የተቀመጡ የሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ አቅጣጫዎች መነሻ በአካባቢዎች የሚታዩ የጸጥታ ችግሮችና የግጭት ትንኮሳዎች በማስወገድ ሰላማዊ አካባቢ ለመፍጠር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
በዚሁ መነሻ በሁሉም የክልሉና አጎራባች አካባቢዎች በተለይም የጸጥታ ግጭት ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት እንደሚደረግ የቢሮ ሃላፊው አስታውቀዋል ።
ከሰላምና ጸጥታ መዋቅር ህጋዊ እርምጃዎች ጎን ለጎን ዘላቂ ሰላምና አብሮነት እንዲፈጠርና አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችሉ የሁለቱም ክልል አጎራባች አካባቢ ትብብር የጋራ መድረኮች ይዘጋጃሉ ሲሉም አቶ ተመስገን ተናግረዋል ።
ውስጣዊ ችግሮችን ከመፍታት ባሻገር ከአጎራባች ክልሎች ጋር በቅርበት በመስራት በማህበረሰቦች መካከል መተማመን እንዲፈጠርና የጸጥታ ስጋቶች እንዲወገዱ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።
የክልሉ ጸጥታ ግብረ ሃይል ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀነራል ተመስገን ማሎሬ ሀገራዊና በሁለቱ አጎራባች ክልሎች የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ግጭቶችን በቅንጅት መፍታት ይገባል፣ በማለት ለዚህም በየደረጃው ያሉ የፀጥታ መዋቅሮች በእቅድ ሊመሩና የመረጃ ልውውጥን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አሳስበዋል::
ብጋዴር ጀነራሉ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ጨምሮ በሌሎች ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉም አክለዋል::
የውይይቱ ተሳታፊዎች የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት በማህበረሰቡ ውስጥ ሆነው ከጠላት ጋር የሚሰሩ ተጠርጣሪዎችን በመለየት ህግ ፊት የማቅረብ፣ ለችግሮችና አለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሄ የመስጠት፣ የአጎራባች አካባቢዎችን የጸጥታ ሁኔታ በቅንጅት መምራት፣ የግጭት ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።


















3ኛው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርቶች ውድድር በቡታጀራ ከተማ ተጀምሯል
#ቡታጅራ | ጥር 14/2018 ዓ.ም
በምስራቅ ጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ
3ኛው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርቶች ውድድር በቡታጀራ ከተማ ተጀምሯል።
የዕለቱ የክብር እንግዶች በቡታጅራ ከተማና የምስራቅ መስቃን ወረዳ እግር ኳስ ውድድር አስጀምረዋል።










የጥምቀት በዓል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ በድምቀት ተከብሮ ዋለ።
#ቡታጅራ | ጥር 11/ 2018
በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ የጥምቀት በዓል ትናንት ከመንበራቸው ወደ ባሕረ ጥምቀት ያመሩት ታቦታት በቅዳሴ፣ በጸሎት እና መንፈሳዊ መዝሙሮች ታጅቦ ጥምቀተ-ባህር ከተከበረ በኋላ ዛሬ በእምነቱ ተከታዮች እጀባና ደማቅ መንፈሳዊ ስነ-ስረዐት ታቦቱ ወደ መንበሩ ተመልሷል።
ለዘወትር ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ከታች ያሉ ገፃቻችንን ይከታተሉ 👇👇follow ያድርጉ!
በዌብሳይታችን https://www.misraqguragezoneprosperityparty.org.et/
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61572637620777
በቴሌግራም
https://t.me/eastguragezoneprosperityinfo
በቲክቶክ
www.tiktok.com/@mesraqguragezonep








የጥምቀት በዓል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል።
ጥር 11/2018 ዓ.ም
በቡኢ ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በተለያየ ሀይማኖታዊ ክዋኔዎች በድምቀት ተከብሮ ዉሏል።
ትላንት ለከተራ በዓል ከክብር ማደሪያቸው ወጥተው ጥምቀተ ባህሩ ላይ ካደሩ ታቦታት መካከል በዛሬው ዕለት የቡኢ ደብረ ሰላም ቅዱስ በዓለ ወልድ በካህናት ዝማሬና በምዕመናን ታጅበው ወደ ደብራቸው በሰላም ተመልሰዋል።
ከዋዜማው ጀምረው በክበረ በበዓሉ ላይ የተገኙት የከተማው ክቡር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ እና የሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ በቴ ጥምቀት ሀይማኖታዊ እሴቶቻችን የሚገለጡበት የማህበራዊ መስተጋብራችን መገለጫ ምልክት እንደሆነ ተናግረዋል።
በመሆኑም ይህንን ታላቅ ሀይማኖታዊ በዓል ስናከብር በፍፁም በአብሮነትና በፍቅር መሆን ይገባል ብለዋል።
ለመላው ምዕመን በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን እንዳስተላለፉ ከከተማው አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
"ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች ለማከናወንና ተማሪዎችን ከእውቀት ጋር የሚያርቅ የመማር ማስተማር ስራ ለመስራት ሚናው የጎላ ነው" ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
(ጥር 10፣ 2018)
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ነጥብ 1ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ማዕከላዊ የአስተዳደር ህንፃ ዛሬ አስመርቋል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ወቅት እንዳሉት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሚያከናውናቸውን የመማር ማስተማር፣ የጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት።
ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች ለማከናወንና ተማሪዎችን ከእውቀት ጋር የሚያርቅ የመማር ማስተማር ስራ ለመስራት ሚናው የጎላ ሲሆን ለምረቃ የበቃው የዩኒቨርሲቲው ማዕከላዊ አስተዳደር ህንፃ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እና ስኬታማ ተግባራት ለማከናወን ያስችለዋል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናና በሌሎችም ዘርፎች የሚያከናውናቸው የምርምር ስራ ውጤቶች ለማህበረሰቡ በማድረስ ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ የተጀማመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
ዩኒቨርስቲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል እየሰራ ያለውን ስራ አበረታች እንደሆነ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ በቀጣይ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል፣ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎች እና የማህበረሰብ አገልግሎት ከመስጠት ጎንለጎን በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ያለውን አስተዋጽኦ ማጉላት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የኢፌድሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ህንፃው የዩኒቨርስቲው ሙህራን የሚያከናውኗቸው የምርምር ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ እውቀታቸውን ተረጋግተው እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል ብለዋል።
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ ከሚገኙ የ3ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ቢሆንም ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ተቋም እንደሆነም ገልፀዋል።
ሀገሪቱ የጀመረችው የኢትዮጵያ ታምርት ኢንሼቲቭ ከግብ ለማድረስ በአምራች ዘርፍ የሚሰማራ የሰው ሀይል ለማፍራት ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ የገለፁት ኮምሽነሩ መንግስት ዲጂታል ኢትዮጵያ ለመገንባት የጀመራቸውን ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ የሚደረግ የምርምር ስራ ማጠናከር ይኖርበታል ብለዋል።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል እንዳሉት ለምረቃ የበቃው ባለ አምስት ወለል ማዕከላዊ ህንፃ የዩኒቨርስቲው ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የቢሮ ጥበትን ያስቀራል ሲሉ ገልፀዋል።
ህንፃው በ7 ሺህ 583 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን 250 ቢሮዎች፣ 400 ታዳሚያን ማስተናገድ የሚችል አንድ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎች እንዳሉት ተናግረዋል።
በግንባታው የጉራጌ ባህላዊ ቤት አጉልቶ የሚያሳይ ዋና መግቢያ እና 33 ሜትር ከፍታ ያለው ክሎክ ታወር የተካተቱ ሲሆን ለግንባታው ከ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መገንባቱ ገልፀዋል።















የቡታጅራ ከተማ ወጣቶች የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራ የፅዳት ስራ አከናወኑ
ጥር 09/2018
የቡታጅራ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ ቤት ከከተማው ወጣቶች ክንፍ ጋር በመተባበር የሦስቱም ቀበሌ ወጣቶችን በማስተባበር የጥምቀት በዓል የሚከበርበት ስፍራ የፅዳት ስራ አከናውነዋል።
ወጣቶቹ "ባህላችንና እምነታችን ውበታችን ነው" በሚል መንፈስ በአሉን አስመልክቶ በማፅዳት ለበዓሉ እንግዶችና ለከተማው ነዋሪዎች ዝግጁ የማድረግ ስራ ሰርተዋል።
የከተማው ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ምንተስኖት እንዳለ የከተማዋ ወጣቶች ለከተማው ውበትና ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ስፍራዎችን ለመንከባከብ ምንጊዜም ዝግጁ ናቸው ብለዋል።
ጥምቀት የሁላችንም ኩራት የሆነ በዓላችን በመሆኑ፣ ስፍራውን ማፅዳት ብቻ ሳይሆን በዓሉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የከተማችንን ሰላም በመጠበቅና እንግዶችን በመንከባከብ የወጣትነት ሚናችንን እንወጣ በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጃቢር ሙዴ ጥምቀት የፍቅር፣ የሰላም እና የወንድማማችነት በዓል ገልፀው ወጣቱ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ እንደነዚህ ባሉ የማህበረሰብ አገልግሎቶች ላይ በንቃት መሳተፉ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ወጣቶች በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ተገኝተው ይህን የበጎ ፈቃድ ስራ መስራታቸው ለሀገርና ለከተማቸው ያላቸውን ክብር ያሳያል ፤ በዓሉም በሰላምና በታላቅ ድምቀት እንዲከበር የድርሻችንን እንወጣለን" ሲሉም አቶ ጃቢር ተናግረዋል።
የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙባረክ ጀማልን ጨምሮ ሌሎች የቀበሌ አመራሮች ተገኝተዋል።














"ሁሉም የክልሉ አካባቢ ባለው ሀብትና ምቹ ሁኔታዎች ልክ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በኢንቨስትመንት እንዲለማ በትኩረት መስራት ይገባል" ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ጥር 9/2018
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ የኢንቨስትመንት አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
ሁሉም የክልሉ አካባቢ ባለው ሀብት፣ የልማት አማራጭና ምቹ ሁኔታዎች ልክ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲለማ በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተናግረዋል ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ የኢንቨስትመንት አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት ባካሄደበት ወቅት እንዳሉት ሁሉም አካባቢ ባለው አቅም ልክ እንዲለማና በሁሉም አካባቢዎች ፍትሃዊ የኢንቨስትመንት ስርጭት እንዲኖር ማድረግ ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ላይዘን ጽ/ቤትን የ6 ወራት አፈጻጸምና ከክልሉ ምስረታ በሗላ በምክር ቤቱ የጸደቁ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ገምግሟል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት የመሬት አቅርቦትና የመሰረተ ልማት ዝርጋታን በማሳደግ እንዲሁም የዘርፉን ማነቆዎች በመፍታት በሁሉም አካባቢ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ የሽርክና ድርጅቶችን ማቋቋም፣ ዳያስፖራውን በስፋት ማሳተፍና የኢንቨስትመንት ስርጭት ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
ከህግና ይገባኛል ነጻ የሆኑ እና ውዝግብ የሌለባቸውን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ማቅረብ ያስፈልጋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር እንዲገቡ ጠንካራ ጥረቶችን ማድረግ ይገባል ሲሉም አክለዋል።
እንደ ክልል በሚቀጥሉት ሶስት ወራት የተለያዩ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ለማስገባት እንደሚሰራም አስታውቀዋል ።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረቡለት የኢንቨስትመንት አጀንዳዎች ዙሪያ በዝርዝር ከተወያየ በሗላ ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እንዲፈጸሙ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል በማለት የዘገበው የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።











"ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)
"ከመስፈንጠር ከፍታ ወደ ላቀ እምርታ" በሚል ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀምን በጉራጌ ዞን አረቅጥ ከተማ እየገመገመ ነው።
ፓርቲው የበጀት አመቱን የመጀሪያ ግማሽ አመት የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል።
በግምገማ መድረኩ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር) በክልሉ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዘርፍ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ተዓማኒና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት እንዲኖረው በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በግምገማ መድረኩ የፓርቲው የበጀት አመቱ የመጀመሪያው ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እየቀረበ ነው።
በመድረኩ በማዕከላዊ ኢትይጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁን አሰፋ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ እንዲሁም ሌሎች የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ የፓርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።












የህዝብን ጥያቄዎች በዘላቂነት ለመፍታት በቅንጅት ርብርብ ማድረግ ይገባል - አቶ አደም ፋራህ
የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በፓርቲና በመንግሥት መዋቅር ቅንጅት በገበያ ማረጋጋት እና ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በንቅናቄ የተሰሩ ተግባራት አፈጻጸም በመገምገምና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በመስጠት ተጠናቋል።
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በማጠቃለያ መድረክ ላይ እንደተናገሩት ገበያውን በዘላቂነት በማረጋጋትና የህዝብን ጥያቄ በዘላቂነት ለመፍታት በቅንጅት በመሰራቱ በዘርፉ አዎንታዊ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
ከዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ በሚፈጠሩ ችግሮች ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በመፍታት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብና ችግሩንም በዘላቂነት ለመፍታት በቅንጅት ርብርብ ማድረግ ይገባል።
ለዚህም ፓርቲው በአመራር ቁርጠኝነት ይሰራል፤ የፓርቲና የመንግሥት መዋቅርም ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
አቅርቦትን በማብዛት፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን ብዛትና ጥራት በማሳደግ፣ የገበያ ማዕከላትን ጥራት በማጎልበት፣ የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት አቅም በማጠናከርና አላስፈላጊ ኬላዎችን በማንሳት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል።
አቶ አደም አያይዘው እንዳነሱት በመደመር መንግሥት ዕሳቤ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ አቅጣጫ መሰረት ያደረገ የክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ስርዓት መከተል ይጠበቃል።
በዚህም በሁሉም ዘርፎች ያሉንን ዕድሎች አሟጦ መጠቀም ይገባል ብለዋል።
የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር የማምጣት ትልም ለማሳካት የክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ በተለይም የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት በሰለጠነ የሰው ኃይል የታገዘ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።
ብዝሃ ተዋንያን መርህ ገቢራዊ በማድረግ የመንግስትና የግል ዘርፍ በቅንጅት በመስራት የስራ ዕድል ፈጠራን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
ለተከታታይ ሶስት ቀናት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ የፓርቲ ስራዎችን በጥልቀት ገምግሟል። የተመዘገቡ አዎንታዊ አፈጻጸሞችን በማስቀጠልና ውስንነቶችን በማረም ለተሻለ አፈጻጸም መትጋት እንደሚገባም አጽንኦት ተሰጥቷል።
#prosperity


















የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር የ2018 በጀት አመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም መገምገም ጀመረ!
#ቡታጅራ | ጥር 08/2018 ዓ.ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር የበጀት አመቱ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ነው።
በአሁኑ ሰዓትም የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ፈለቀ አስፋው በዞኑ በ2018 በጀት አመት እስካሁን የተከናወኑ የ6 ወራት እቅድ አፈፃጸሞች ሪፖርርት እያቀረቡ ነው።
በመድረኩም በዋናነትም በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ አባይት ተግባራት ተገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል ።
በመድረኩም የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ደሴ አበጋዝ እና የመምሪያና የጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።












የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልፅግና ኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚሽን የበጀት ዓመቱን የ6/ስድስት/ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ፣
#ቡታጅራ| ጥር 07/2018 ዓ/ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የከተማና የወረዳ የኮሚሽኑ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በቡታጅራ ከተማ ገምግሟል።
ሰባቱም የወረዳና የከተማ አስተዳደር የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤቶች በመድረኩ ሪፓርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በዚሁ መነሻ ውይይት ተካሂዶበታል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ም/ዋና ኮሚሽነር አዳነ ተሰማ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት በየግዜው ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የሚያስችል አንስፔክሽን ማድረግና የስነ-ምግባር ክትትል ማድረጋችን በዞናችን ብሎም በዞኑ ስር ባሉ መዋቅሮች ለፓርቲያችን ከፍተኛ ፋይዳ ያስገኘ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አውስተው በቀጣይም ይህንኑ አጠናክረን ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ አዳነ ተሰማ አክለውም እንዳሉት ከዕቅድ አኳያ አፈፃፀሙ በመዋቅሮች መካከል የአፈፃፀም ልዩነት ቢኖርም በጥቅሉ ሲታይ የተሻለ አፈፃፀም እየታየ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም መዋቅር የተሰጡትን አስተያየቶች ለቀጣዩ የስራ ግዜ እንደግብዐት ወስዶ መስራት እና ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የሚያስችል ተግባር ማከናወን ይገባል በማለት አስገንዝበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ፅ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ አሰፋ ፈይሳ በበኩላቸው ቀደም ሲል የግማሽ ዓመቱን የአፈፃፀም ደረጃ በሁሉም መዋቅር በኢንስፔክሽን ማረጋገጥ የተቻለ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ደግሞ ከሁሉም መዋቅር ከቀረበው ሪፓርት መረዳት እንደተቻለው የተሻለ አፈፃፀም እየተመዘገበ መሆኑን መረዳት እንደተቻለ ገልፀዋል።
ኃላፊው አቶ አሰፋ አክለውም እንዳሉት የዛሬው መድረክ ለቀጣይ ተግባር ስንቅ የሚሆን መነሻ የተያዘበት ሲሆን በቀጣዩ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ግማሽ ዓመት የስራ ግዜያት በዞኑ ስር ያሉ የኮሚሽኑ አደረጃጀቶችን በተሻለ ቁመና ወደስራ በማስገባት የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች ስራ ላይ መዋላቸውን መከታተል፣ የፓለቲካ ጥራትና ስነምግባር መከታተል እና መሰል የኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነትን በአግባቡ በመወጣት ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት በሚያስችል መልኩ ወጤታማ ተግባር ማከናወናችንን መቀጠል ይኖርብናል በማለት አስገንዝበው መድረኩን ማጠናቀቅ ተችሏል።













የብልጽግና ፓርቲ የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው
(ጥር 6/2018)
የብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት ያለፉትን ስድስት ወራት የፓርቲ ስራዎች በመገምገም ተሞክሮ መለዋወጥ የሚያስችል መድረክ ነው ብለዋል።
ፓርቲው በሀገር አቀፍ ደረጃ በዋና ዋና የፓርቲ ስራዎች ያከናወናቸውን ተግባራት ይገመግማል፡፡
በሂደት የገጠሙንን ተግዳሮቶች ለመፍታት የጋራ ተግባቦት በመፍጠር በላቀ ቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉም አቶ አደም በንግግራቸው ጠቁመዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን መድረኩ በፓርቲው ሚናዎች ላይ በስፋት ይመክራልም ነው ያሉት።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም በልማት ተምሳሌት መሆን ችሏል ያሉት አቶ አደም÷ ለዚህም የፓርቲው የአመራር ቁርጠኝነትና የሕዝብ ተሳትፎ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አብራርተዋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) እንደገለጹት ክልሉ ሲመሰረት በበርካታ ውስብስብ ፈተናዎች ውስጥ በማለፍ ነው ብለዋል።
በክልሉ ከ60 ሺ በላይ ሰራተኞች እንደነበሩ ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ በአንድ አንድ አካባቢዎች ደመወዝ በተገቢው መንገድ መክፈል አለመቻሉን ጠቁመዋል።
ግንባታቸው የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በክፍያ ምክንያት የተቋረጡበት፣የማዳበሪያ እዳ ፣ከ6ቢሊየን በላይ ብር የፌደራል መንግስት እዳና የሰራተኛ የጡረታ ብር ገቢ ያለመሆንችግሮችን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መቀዛቀዝ፣በርካታ አመራር በክልል አደረጃጀት ጥያቄ አጀንዳ ውስጥ መሆን፣የስራ መቀዛቀዝ የክልሉ ሰራተኞች ወደ ተመደቡባቸው አካባቢዎች ያልተጓጓዙበት እና የቢሮ ዝግጅት ያልነበረበትን ጊዜ ርዕሰ መስተዳድሩ በተግዳሮትነት ጠቁመዋል።
ክልሉን በአመራር እና በሰራተኛ ከማደራጀት በተጓዳኝ በሰባቱ የክልል ማዕከላት ቢሮ በመከራየት ወደ ስራ መገባቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል የሰላም፣የገቢ፣የትምህርት፣የጤና የስራ እድል ፈጠራ፣ የኑሮ ማረጋጋት ስራዎች እንዲሁም የኢንቬስትመንት እና የመሰረተ ልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በሁሉም መስክ ከፍተኛ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ወደ ተግባር በመገባቱ ከነበሩት ችግሮች መላቀቅ ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የአዳዲስ ፕሮጀክቶች ግንባታ ስለመጀመሩም አስተውሰዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር )እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ከሰው ልጆች ሁለንተናዊ ባህሪ የሚነሳና የሰው ልጆችን የነጻነት፣የእኩልነት እና መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ሚዛን በጠበቀ ሁኔታ ማሟላት ይገባል ብሎ የሚያምን ፓርቲ ነው ብለዋል።
በሀገሩቱም ሆነ በክልሎች በተቋም ግንባታ ማዕቀፍ ውስጥ የተቋማዊ አሰራር ባህል ለመገንባት የሚሰራ ተራማጅ ፓርቲ ስለመሆኑም ዶ/ር ዲላሞ አብራርተዋል።
የዲሞክራሲ አመራር መርህን በመከተል ሰላማዊና የተረጋጋች ሀገር ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ ዘመን ተሻጋሪ ራዕይ በመንደፍ እየተንቀሳቀሰ ያለ ፓርቲ ነው ሲሉም ዶ/ር ዲላሞ ጠቁመዋል።
ክልሉ ሰፊ ብዝሀነት ያለው እንደመሆኑ በአንድ በኩል ብዝሀነትን በአግባቡ የሚያስተናግድ እና በሌላ በኩል ደግሞ የህዝባችንን አንድነት የሚያረጋግጥ እውነተኛ ህብረ ብሔራዊ ፌደራላዊ ስርዓት በክልሉ እውን ለማድረግ መጠነ ሰፊ ስራ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊው አስረድተዋል በማለት የዘገበው የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።
ለዘወትር ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ከታች ያሉ ገፃቻችንን ይከታተሉ 👇👇follow ያድርጉ!
በዌብሳይታችን https://www.misraqguragezoneprosperityparty.org.et/
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61572637620777
በቴሌግራም
https://t.me/eastguragezoneprosperityinfo
በቲክቶክ
www.tiktok.com/@mesraqguragezonep















"በምስራቅ ጉራጌ ዞን ያየናቸው የልማት እንቅስቃሴዎች የፓርቲውን የብዝሃ ተጠቃሚነት የኢኮኖሚ አቅጣጫ ውጤታማነት አመላካች ናቸው" አቶ አደም ፋራህ
#ቡታጅራ | ጥር 5/2018
የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በቡታጅራ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ ያየናቸው የልማት እንቅስቃሴዎች የፓርቲውን ብሎም የመንግስትን የብዝሃ ተጠቃሚነት የኢኮኖሚ አቅጣጫ ውጤታማነት አመላካች ናቸው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።
በአቶ አደም የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ እየተካሄዱ የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርጓል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በቡታጅራ ከተማ የወንዝ ዳርና ኮሪደር ልማት፣ የሌማት ትሩፋት፣ የደስታ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታው የፌደራል፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
አቶ አደም በዚሁ ወቅት ክልሉ እንደ አዲስ ሳይሆን በተነቃቃ ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። በተለይም በቡታጅራ ከተማ የተመለከትናቸው የልማት ተግባራት የመንግሥትን የልማት አቅጣጫዎች ስኬት አመላካች ናቸው ሲሉም አክለዋል።
በአካባቢው የሚታዩት የአረንጓዴ አሻራ፣ የኮሪደር ልማት፣ የሌማት ትሩፋት ስራዎች አበረታች መሆናቸው ገልጸዋል ።
የአቮካዶ ኤክስፖርት ፣ የሌማት ትሩፋት የወተት፣ የማር፣ የዶሮና እንቁላል ምርቶች የህብርተሰቡን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በማስፋት ረገድ ትልቅ ሚና እየተወጡ እንደሆነም አስረድተዋል ።
የሌማት ትሩፋት ዘርፍ በስራ እድል ፈጠራና በዜጎች የገቢ ምንጭነት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑንም አቶ አደም ተናግረዋል።




























ሳምንታዊ መልዕክት
ሀገራዊ ለውጡ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምህዳር በማስፋት ለእውነተኛ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በር የከፈተ ታሪካዊ ክስተት ነው።
ሀገራዊ ለውጡ በግንባር ቀደምትነት ከመለሳቸው ህዝባዊ ጥያቄዎች አንዱና ዋነኛው የሀገራችንን የፖለቲካ ምህዳር ማስፋትና የዴሞክራሲ ሥብራቱን መጠገን ነው፡፡ ይህ ለዘመናት ሲንከባለል የቆየው የህዝቦች የዴሞክራሲ መሻት ትርጉም ባለው መልኩ ለማርካት ከዚህ በፊት ያልተሄዱባቸው አዳዲስ መንገዶችና ያልተደፈሩ ቆራጥ እርምጃዎችንና ንቅናቄዎችን ተግባራዊ በማድረግ የታሪክ እጥፋት መፍጠር ተችሏል፡፡
ይህ የታሪክ እጥፋት በህዝብ የውጭ ግፊትና በአመራር የውስጥ ሳቢነት እንዲሁም በለውጥ ፈላጊ ኃይሎች ተባባሪነት የተፈጠረ ነው፡፡ እጥፋቱ በቅድሚያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የበላይ አመራሮች ሽግግርና የሥርዓት ማሻሻያ ማሳካት ተችሎበታል፡፡ በመቀጠል ደግሞ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ነጻ የማውጣት፣ በስደት የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አመራሮቻቸው በክብር ወደ ሀገራቸው የመመለስ፣ የትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ የቆዩ አካላት ከህዝባቸው ጋር በሰላም እንዲኖሩ የማድረግና የልማት ኃይል ሆነው እንዲቀጥሉ የማስቻል እንዲሁም መላ የሀገራችን ህዝብ በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ ተስፋው እንዲለመልም ተደርጓል፡፡
ይህ ተስፋ ዘላቂነት እንዲኖረው ለማስቻል አያሌ የዕሳቤ ለውጦች፣ የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች፣ የተቋም ግንባታዎች እና አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ ሀገራዊ መግባባት፣ የሰፋ ፖለቲካ ምህዳር እና የተረጋጋ ሰላም እዉን ለማድረግ ተችሎበታል፡፡ ለውጡ ይህን ሁሉ ሲያሳካ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም፤ ይሁንና በተለያዩ የፈተና ወጀቦች ውስጥም ሆኖ የተነሳበትን ሀገራዊ ዓላማ ሲያሳካ ቆይቷል፡፡
ለአብነት “ተቃዋሚ” በመባል ይጠሩ የነበሩ የፖለቲካ ኃይሎች “ተፎካካሪ” በሚል ዴሞክራሲያዊና ዘመናዊ ስያሜ በማስተናገድ በፉክክርና በትብብር መካከል ሚዛን እንዲኖር በማድረግ የተደመረና የተባባረ ጠንካራ የዴሞክራሲ ሥርዓት እዉን ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህ ሁኔታ ፖለቲካችን እንዲሰክን ያደረገ ብቻ ሳይሆን በትብብር መሥራት እንደሚቻል ያሳየ አዲስ ታሪክ ነው፡፡ ይህ ትብብርም በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በጉልህ የታየ ሲሆን መንግሥት ለህዝብና ለለውጥ ኃይሎች የገባውን ቃል በመጠበቅ 275 የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራር በተለያዩ የመንግሥት የኃላፊነት እርከኖች እንዲመሩ በማስቻል ኢትዮጵያውን መተባበር የሚችሉ የአንድ ሀገር ልጆች መሆናቸውን በተግባር አስመስክረዋል፡፡
ይህ የትብብር መንፈስ በዘንድሮው 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ላይም ለመድገም ከማንኛውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ መደላድል ተገንብቷል፡፡ በዚህ መሠረት ሀገራዊ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሀዊ፣ አሳታፊና ተአማኒ ከማድረግ በተጨማሪ የመላው ኢትዮጵያውያን የላቀ ትብብርና አንድነት ተጨማሪ መገለጫ እንዲሆን እየተሰራበት ይገኛል፡፡
ስለሆነም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዚህ የላቀ የዴሞክራሲ ዓላማ በምልዓት መሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበርክት ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
ብልፅግና ፓርቲ
ጥር 04፤ 2018 ዓ/ም
#prosperity

የአብሮነትና የወንድማማችነት ማሳያ፤ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ለሀላባ ህዝብ የ"ሴራ" በዓል ስጦታ አበረከተ
የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ እና የማንነት መገለጫ የሆነውን የ"ሴራ" በዓል በድምቀት እያከበረ ይገኛል።
ይህንን ታላቅ በዓል ምክንያት በማድረግ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በበዓሉ ላይ በመገኘት የአጋርነትና የወንድማማችነት ስጦታ አበርክተዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ለሀላባ ህዝብ ያለውን አክብሮትና ጥልቅ ትስስር ለመግለጽ በዕለቱም ስጦታዎች አበርክቷል።
በዩኔስኮ የተመዘገበውንና የምስራቅ ጉራጌ ዞን መለያ የሆነውን የጥያ ትክል ድንጋይ ምስል/ቅርጽ እና ሰነጋ በስጦታነት አቅርቧል።
ይህ ስጦታ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን የባህልና የታሪክ ትስስር የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
የስጦታ ርክክቡ ወቅት እንደተገለጸው፣ የ"ሴራ" በዓል የሰላም፣ የፍትህና የዕርቅ በዓል በመሆኑ፣ ይህ ስጦታ በሁለቱ ጎረቤት ህዝቦች መካከል ያለውን ማህበራዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ታምኖበታል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በመልዕክታቸው እንዳሉት "ባህላዊ እሴቶቻችን የጋራ ቤታችን መገንቢያ ናቸው" በሚል መልዕክት ለሀላባ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ አስተላልፏል።
የሀላባ ዞን አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ላሳየው ወንድማማችነትና ላበረከተው ስጦታ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል
በዓልን በስጦታ፤ ወንድማማችነትን በተግባር!
ለዘወትር ፈጣንና ትኩስ መረጃ ከታች ያሉ ገፃቻችንን ይከታተሉ 👇👇follow ያድርጉ!
በዌብሳይታችን https://www.misraqguragezoneprosperityparty.org.et/
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61572637620777
በቴሌግራም
https://t.me/eastguragezoneprosperityinfo
በቲክቶክ
www.tiktok.com/@mesraqguragezonep













የምስራቅ ጉራጌ ዞን የወጣት አደረጃጀቶች የገና በዓልን አስመልክቶ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ማዕድ በማሰባሰብ ድጋፍ እንዲያገኙ አደረጉ
#ቡታጅራ ታህሳስ 28/2018
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የወጣት አደረጃጀቶች የገና በዓልን አስመልክቶ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በሚል ያሰባሰቡትን ማዕድ ያቀረቡ ሲሆን፤
አቶ መሰረት ሽፋ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪና የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የወጣት አደረጃጀቶች ያሰባሰቡትን ማዕድ አጋርተዋል።
አቶ መሰረት ሽፋ ማዕዱን ካጋሩ በኋላ እንዳሉት ፓርቲያችን ብልፅግና ሰው ተኮር እንደመሆኑ መተጋገዝንና መተባበርን ያበረታታል ያሉ ሲሆን አክለውም የዞኑ ወጣቶች ከተለያየ ማህበረሰብ አሰባስበው ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በሚል በማሰባሰባቸው ያላቸውን ምስጋና ገልፀው ይህ አርአያነት ያለው ተግባር በሌሎች አካባቢዎችም ሊለመድና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በዛሬው ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም ላይ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማረ ዓለሙ፣ በዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ አቶ ነቢል ሻንቆ እና ረቢል ከድር የምስራቅ ጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ተገኝተዋል።
ለዘወትር ፈጣንና ትኩስ መረጃ ከታች ያሉ ገፃቻችንን ይከታተሉ 👇👇follow ያድርጉ!
በዌብሳይታችን https://www.misraqguragezoneprosperityparty.org.et/
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61572637620777
በቴሌግራም
https://t.me/eastguragezoneprosperityinfo
በቲክቶክ
www.tiktok.com/@mesraqguragezonep












"የገዢ ትርክት የበላይነትን መጎናጸፍ ፣ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥና ለሴቶች የኢኮኖሚ ተሳትፎ" በሚል መሪ ሀሳብ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ
#ቡታጅራ ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት በዞኑ "የገዢ ትርክት የበላይነት መጎናፀፍ ፣ለዘላቂ ሠላም ማረጋገጥ እና ለሴቶች የኢኮኖሚ ተሳትፎ" በሚል መሪ ሀሳብ ያተኮረ የውይይት መድረክ በቡታጅራ ከተማ ተካሄዷል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማረ አለሙ የገዢ ትርክት ግንባታን በማጠናከር የህዝቦችን እርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፏል።
በህዝቦች መካከል አብሮነትንና አንድነት ለማጠናከር የፀረ ሰላም ሃይሎችን መመከት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የተጀመረውን ልማትና የብልፅግና ጉዞ ላይ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ነጠላ ትርክትን በማረቅ ይልቁንም የወል እሴቶችን በማጠናከር የገዢ ትርክት ለማስረፅ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የትምወርቅ ንጉሴ ገዢ ትርክት በማስረፅ እንደሀገር የተጀመረውን የሀገረ መንግስት ግንባታ ውጤታማ እንዲሆን ሴቶች ትልቁን ድርሻ እንዳላቸው ገልፀዋል።
ነጠላ ትርክት ለዘመናት ጥላቻና ለእርስ በርስ ግጭት ምክንያት በመሆን ከፍተኛ ችግሮች እንዲያጋጥመን እያደረገ መሆኑን አንስተው ሴቶች አብሮነትና አንድነት እንዲጎለብት አሰባሳቢ ትርክትን ከፍ በማድረግ ለአካባቢ ሰላም እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
በዞኑ የሴቶችን አቅም በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊና ፖለቲካ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት የሚያረጋግጡ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አንስተዋል።
የሴቶች አደረጃጀቶችን በማጠናከር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነታቸውን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቡታጀራ ክላስተር የክልል ተቋማት የብልጽግና የሴቶች ክንፍ ህብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ እናትዓለም ሀብተማርያም ሴቶች እንደሀገር የገዢ ትርክት በቤተሰብ ውስጥ ጀምሮ በማስረፅ ውጤት እንዲያመጣ ትልቁ እድል እንዳለቸው ተናግረዋል።
የነገው ትውልድ ልጆችን የመቅረፅ ኃላፊነት የሚወጡት ሴቶች በመሆናቸው ትውልድ ሀገራዊ ስሜትና የጋራ ትርክት ትኩረት እንዲያደርግ የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል።
በመድረኩ የክልሉ የቡታጅራ ክላስተር፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ማዕከል፤ የከተማና የወረዳ የሴቶች ክንፍ ኃላፊዎች፣የሴቶች ማህበር፣ የፌደሬሽን፣ የቤተሰብ ሰብሳቢዎች፣ ሴት አመራርችና ሲቭል ሰርቫንቶችና ሌሎችም ተሳትፈዋል።
ለዘወትር ፈጣንና ትኩስ መረጃ ከታች ያሉ ገፃቻችንን ይከታተሉ 👇👇follow ያድርጉ!
በዌብሳይታችን https://www.misraqguragezoneprosperityparty.org.et/
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61572637620777
በቴሌግራም
https://t.me/eastguragezoneprosperityinfo
በቲክቶክ
www.tiktok.com/@mesraqguragezonep













"የዞናችን የወጣቶችና ሴቶች በፖለቲካው መድረክ የመሳተፍ ሚናቸው ጨምሯል" አቶ አማረ ዓለሙ
#ቡታጅራ| ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶችን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር የሚያስችል የውይይት መድረክ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል።
በዚሁ መድረክ ላይ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አማረ ዓለሙ በዞችን የወጣቶችና ሴቶች በፖለቲካው ውስጥ የመሳተፍ ሚናቸው ጨምሯል ብለዋል።
አካታችና የበለፀገ ህብረተሠብ መገንባት የሚቻለው ሞዴሎችን በሁሉም አደረጃጀቶች በማብዛትና ተጠቃሚነታቸውን በማጠናከር ሲሆን ይህንኑ ግብ ለማሳካት የዞኑ ፌዴሬሽኖች፣ ማህበራትና የክንፎች አመራሮች ሚና ወሳኝ ነው በማለትም ተናግረዋል።
ዞናችን ከተደራጀ በቅርብ ቢሆንም በብዙ ተግባሮች አፈፃፀም ግንባር ቀደም መሆን መቻሉን የገለፁት አቶ አማረ በወጣቶችና ሴቶች ተሳትፎዎች የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን ቀጣይነት እያረጋገጡ በመሄድ የወጣቶችን እና የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያሳደጉ መሄድ ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል።
የወጣቶችን ተወዳዳሪነት ማሳደግ የሚቻለው ወጣቶችን በዕውቀት ፣ በክህሎትና በስነ-ምግባር የመገንባት ድርሻችንን መወጣት ስንችል ነው በማለት የተናገሩት አቶ አማረ ለዚህም የዘርፎቹና የባለ ድርሻ አካላት ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ ከፍ ያለ ድርሻ ያለው መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የወጣቶችና ሴቶች ፌዴሬሽኖችን፣ ማህበራትና ክንፎችን በማጠናከር በሀገር ግንባታ፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችና ተሳትፎዎች ላይ ያሏቸው አቅሞች እየጎለበተ መሄድ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉም አሳስበዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎቹ የወጣቶችና ሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነቶች ለማረጋገጥ በሚደረጉ ወሳኝ ሀገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ ሁነቶች ላይ ተቀናጅቶ በመስራት፣ ብቁ የሆኑትን የወጣትና ሴቶች አደረጃጀቶቻችንን አቅሞች ከመጠቀም ጎን ለጎን ያሉብንን ክፍተቶች እየሞላን መሄድ አለብን ብለዋል።በመድረኩ ላይ የዞኑ ሴቶችና ወጣቶች ፌዴሬሽኖች ፣ ማህበራት ፣ እንዲሁም የክንፎች አመራሮች ተሳትፈዋል።





"ገዢ ትርክትን በማህበረሰቡ ውስጥ በማስረፅና ህዝቡን ለልማት ስራ አነሳስቶ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማሳካት ሚዲያ የማይተካ ሚና አለው" አቶ መሰለ ጫካ!
#ቡታጅራ| ታህሳስ 22/2018
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሚዲያ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት መደበኛ ውይይቱን አካሂዷል።
በመድረኩ በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ተግባራት ቀርበው የተገመገመ ሲሆን በዋናነት ወሳኝ መልዕክቶችን ቀርፃ ከማስተላለፍ፣ ገዢ ትርክትን ከማስረፅ አኳያና ፈጣንና ትኩስ ዜናዎችን በተለያየ የሚዲያ አማራጮች ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
አቶ መሰለ ጫካ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ እና የዞኑ ሚዲያ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደገለፁት ገዢ ትርክትን በማህበረሰቡ ውስጥ በማስረፅና ህዝቡን ለልማት ስራ አነሳስቶ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማሳካት ሚዲያ የማይተካ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ሚዲያችን በዞን ደረጃ ይህንን ተልዕኮ ከመወጣት አኳያ ያሉ መልካም አፈፃፀሞችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከመቼውም ግዜ በላይ ባሉ የሚዲያ አማራጮች ሁሉ በመጠቀም ተደራሽነትን አስፍቶ መስራት ይገባል ካሉ በኋላ አክለውም እንዳሉት ከሰው ኃይልና ከቁሳቁስ አኳያ ያሉ ጉድለቶችን በሂደት እየሞሉ መሄድ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል በማለት አስገንዝበዋል።
አቶ መሰረት ሽፋ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የዞኑ ሚዲያ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ በበኩላቸው እንዳሉት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ረገድ እየተሰሩ ያሉ መልካም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ በተናበበና በተቀናጀ ሁኔታ በየፕላትፎርሙ ፈጣንና ተደራሽ የሆነ መረጃን በህዝብና በመንግስት መካከል ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም ኮሚቴው በየግዜው እየተገኘ ተግባርን መገምገም ስለሚቻልበት ሁኔታ ላይ መግባባት በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል።





ሀገር የምትለወጠው ጠንክሮ በመስራት ብቻ ነው:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)
(ታህሳስ 22/2018)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ከዱራሜ ክላስተር አመራሮች እና የማኔጅመንት አካላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ሀገር የምትለወጠው ጠንክሮ በመስራት ነው ብለዋል።
ክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ ለማጠናቀቅ በወሰደው ቆራጥ ውሳኔ የላቀ ውጤት ስለመመዝገቡም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።
በክልሉ በሁሉም ክላስተሮች የቢሮ ግንባታ ስራ በጊዜ ተጀምሯል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም በቢሊየን የሚቆጠር ሀብት ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል።
ሀገር የምትለወጠው በስራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሁሉም በተሰማራበት መስክ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል።
የክልሉ መንግስት ሙሉ ጊዜውን በስራ ላይ በማዋል የህዝብ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል በማለት የዘገበው የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።














በክልሉ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ እየተካሔደ ያለው የልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)
ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)የዞኖችን እና የልዩ ወረዳዎችን የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)በምክክር መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ ላይ እንደገለጹት በክልሉ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ እየተካሔደ ያለው የልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
ምርታማነት መጨመር ላይ የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
በቅመማ ቅመም ዘርፍ ሮዝመሪ እንዲሁም ባህርዛፍን በማንሳት ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ያላቸውን የግብርና ስራዎች ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉም ጠቁመዋል።
የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መቅረፍ ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል።
የሌማት ትሩፋት ምርታማነትን በማሳደግ ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ይገባል ሲሉም አስረድተዋል።
በገቢ አሰባሰብ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ለአመቱ የተያዘውን ግብ ማሳካት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ስኬታማ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ያሻዋል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
መሬት ወስደው ወደ ልማት ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ ክትትል በማድረግ ዘርፉን መፈተሽ ተገቢ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
አርሶ አደሩ ከፋይናንስ ተቋማት ብድር እንዲያገኝ በማድረግ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የተጀመረውን የከተማ ኮሪደር ልማት ስራ እስከ ሰኔ 30/2018 ድረስ ለማጠናቀቅ መስራት ይገባል ብለዋል።
በነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭት ላይ የሚስተዋለውን ህገወጥነት መከላከል ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
በመሬት ላይ የሚስተዋለውን ህገወጥነት የመከላከሉ ስራ የሁሉንም አካላት ጥረት ይጠይቃል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።



በምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት የ2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ ድጋፍ ለማድረግ ለድጋፍና ክትትል ቡድን ስምሪት ሰጠ፤
#ቡታጅራ| ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ 2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ በዞኑ ውስጥ ወደሚገኙ ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮቹ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ በሚያስችል በተዘጋጀ ቼክሊስት ላይ ለዞኑ የክንፉ ስራ አስፈፃሚዎች ገለፃ/orientation በመስጠት ስምሪት ሰጥቷል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወጣት ነቢል ሻንቆ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ በሚያስችል በተዘጋጀ ቼክሊስት ላይ በዛሬው ዕለት ከዞኑ የክንፉ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት ተደርጎበት የጋራ መደረግ መቻሉን ገልፀዋል።
ኃላፊው ወጣት ነቢል ገለፃውን/orientation/ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት የበጀት ዓመቱን 2ኛ ሩብ ዓመት እያገባደድን እንደመሆኑ በሰባቱም መዋቅሮች በወጣቶች ክንፍ ያሉ የአፈፃፀም ደረጃን ማወቅ እና ጠንካራ አፈፃፀሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፤ ውስንነቶች ካሉም በቀጣይ ጊዜያት በበቂ ሁኔታ በማካካስ እንዲፈፅሙ የድጋፍና ክትትል ቡድኑ አስተማሪ ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል።
በመድረኩ በቼክሊስቱ ላይ የጋራ መረዳት ከተፈጠረ በኋላ በዞኑ ስር ወደሚገኙ ወደሰባቱም የክንፉ መዋቅሮች ለዞኑ የወጣት ክንፍ ስራ አስፈፃሚዎች ስምሪት የተሰጠ ሲሆን ከነገው ዕለት ጀምሮ የድጋፍና ክትትል ስራው እንደሚጀምር መረዳት ተችሏል።





"በየደረጃው የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን እያጠናከሩ መሄድ ለልማትና መልካም አስተዳደር ስኬታማ አፈፃፀም ወሳኝ ነው"
አቶ መሠለ ጫካ
#ቡታጅራ| ታህሳስ 20/2018 ዓ/ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ፓርቲ ስራ አመራር ኮሚቴ ወቅታዊ የፓለቲካ ነባራዊ ሁኔታ እና የበጀት ዓመቱ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም በዛሬው ዕለት በቡታጅራ ከተማ ገምግሟል።
በመድረኩ በፓርቲ መሪነት በንቅናቄ የሚፈፀሙ መንግስታዊ ተግባራት ማለትም በገቢ አሰባሰብ፣ በንግድና ገበያ ልማት የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ፣ በግብርና በተለይም ከተረጂነት ወደ ምርታማነትና የበጋ ስንዴ ፣ ከጤና አኳያ የማዕጤመ፣ ከትምህርት፣ ከስራ ዕድል ፈጠራ እና ከፋይዳ መታወቅያ አፈፃፀም አንፃር ሪፓርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን ከመደበኛ የፓለቲካ ስራዎች አኳያ በሁሉም መዋቅር የፓርቲ አደረጃጀቶች ቁመና እና በአደረጃጀትና አሰራር መመሪያው መሰረት የተግባር አፈፃፀማቸው በበጀት ዓመቱ የ6/ስድስት/ ወር ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
አቶ መሠለ ጫካ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ ከሪፓርቱ በኋላ ውይይቱን ሲያስጀምሩ እንደገለፀለት ከመቼውም ግዜ በላይ በየደረጃው በፓርቲያችን አመራርና አባል ዘንድ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነታችንን እያጠናከሩ መሄድ ለልማትና መልካም አስተዳደር ስኬቶቻችን ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን ይህንንም ከእያንዳንዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ውጤቶች ጋር በማስተሳሰር ነባራዊ ሁኔታን መረዳት ብሎም ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም፤ የተገኙ ውጤቶችን ደግሞ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ያሉ ሲሆን፣
ከዚህ በተጨማሪም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የተቀመጡ ማለትም፣ የመቀነስ፣ የዜሮ የ100% ግብ ዕቅዶች በሁሉም ሴክተር በልዩ ትኩረት እና በላቀ ደረጃ በመፈፀም የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አቶ መሰረት ሽፋ የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ በበኩላቸው የተመዘገቡ አፈፃፀሞችን ፍጥነትና ፈጠራን በማከል በተሻለ ሁኔታ ማስቀጠል፤ እንዲሁም የአባላት የዕለት ተዕለት ግንባታን ማጠናከርና ፓለቲካል አዝማሚያንና ነባራዊ ሁኔታን እየገመገሙ መሄድን አጠናክረን ማስቀጠል እና የህዝባችንን ሰላም የሚነሱትን ሀይሎች ለማረምና እርምጃ ለመውሰደድ በተደራጀና በተናበበ ሁኔታ ከህዝባችን ጋር በመሆን የምንሰራውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
አቶ አህመድ ኑሪ የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በበኩላቸው ያለንበት አፈፃፀም የተሻለ ሲሆን ይህ ዓመት ምርጫ የምናካሂደበትም ዓመት እንደመሆኑ በየመዋቅሩ ያሉ አደረጃጀቶችን ማጠናከርና መደበኛ የፓርቲ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን በየአካባቢው እየተፈጠረ ያለውን የሰላምና ፀጥታ ችግር ለመፍታትም ከህዝባችን ጋር ሆነን መዋቅሮቹን በመደገፍ እየተሰራ ያለውን ስራ ከወትሮው በላቀ ዝግጁነት የምንቀጥል ይሆናል ብለዋል።
በመጨረሻም በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሠለ ጫካ እንዳሉት ከቀረበው ሪፖርት እንደታየው በሁሉም ዘርፍ በስድስት ወሩ ከዕቅድ አኳያ የዞናችንን ማህበረሰብ የጠቀሙ፣ በዞኑ አቅዶ የመፈፀም አቅም የታየባቸው ዞኑን የተሞክሮ ማዕከል ማድረግ የቻሉ ብዙ ውጤቶች መኖራቸው የማይካድ ሃቅ ቢሆንም ህዝባችንን ከሰላማዊ ኑኖውና ከልማት ስራው የሚነጥሉ አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው፣ የዞኑን ሰላምና ፀጥታ የሚያውኩ ኃይሎችን የመመከትና የማረም ስራዎች በተናበበ የአመራር ስርአት በመፈጸም ህዝባችንን እያስተባበርን ከመቼውም ግዜ በላይ በንቃት መስራት ይገባል በሚል ያሳሰቡ ሲሆን በተጨማሪም የቀጣይ የስራ መመሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ::







መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ማጠናከር ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስን ለመገንባት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑ ተገለፀ::
(ታህሳስ 17/2018)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በከተሞች ለማስፋት የሚያስችል ስልጠና ለዘርፉ አመራሮችና ባለሞያዎች በሆሳዕና ከተማ ተሰጥቷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ በስልጠናው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ማጠናከር ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስን ለመገንባት አስተዋጽኦው የጎላ ነው ብለዋል።
ማዕከሉን በ7 የክልል ክላስተር ከተሞች እና በ10 የከተማ አስተዳደሮች ለማስፋፋት እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ገብሬ ስልጠናው በቴክኖሎጂ ፣ በኮንስትራክሽን ፣በአገልግሎትና በሰው ሀብት ልማት ዘርፎች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተናግረዋል።
ስልጠናው ማዕከላቱን በታለመለት ጊዜ በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ለማስጀመር አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረው ማዕከሉ የተበታተኑ የመንግስት አገልግሎቶችን በአንድ በማሰባሰብ የክልሉን ልማት ያፋጥናል ብለዋል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ በ7 የክልል ክላስተር ከተሞች ጥር 30//2018 አገልግሎት እንዲሰጥና ሁለተኛው ምዕራፍ በ10 ከተሞች መጋቢት 30/2018 ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አቶ ገብሬ ተናግረዋል።
ማዕከሉ የዜጎችን አገልግሎት የማግኘት መብት የሚያረጋገጥ መሆኑንም ሀላፊው ገልፀዋል።
የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው መንግስት በሳይንስ ፣በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ሪፎርሙ ቴክኖሎጂ የሁሉንም ዘርፎች ስራ ማገዝ እንዲችል እየሰራ ነው ብለዋል።
ዲጂታል አገልግሎትን መጠቀምና መስጠት የሚችል ዲጂታል ማህበረስብ በመፍጠር በማዕከሉ የዜጎችን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን አቶ ሰላሙ ተናግረዋል።
የክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ሻሜቦ ማዕከሉ ከመስከረም 15/2018 ጀምሮ ከ7 መስሪያ ቤቶች 20 አገልግሎቶች እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ከ4ሺ በላይ አገልግሎት ለተገልጋዮች ማቅረብ መቻሉን የገለፁት አቶ ከበደ አገልግሎቱን በስታንዳርድ በማቅረብ የተገልጋይ እርካታን ከ97 በመቶ በላይ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል።
መሶብ ለተገልጋይ ፈጣን ምላሽ የሰጠ ማዕከል ነው ያሉት ስራአስኪያጁ ማዕከሉ የተገልጋይ ጊዜን ፣ገንዘብና ጉልበት በመቆጠብ ጥራት ያለው ደህንነቱ የተጠበቀ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት መፍጠር አስችሏል ማለታቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ገፅ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።









የኢንስፔክሽን ቡድኑ በቡታጅራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሲያደርግ የቆየውን የኢንስፔክሽን ስራ ጨርሶ የማጠቃለያ ግብረ-መልስ በመስጠት አጠናቀቀ፤
#ቡታጅራ | ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የኢንስፔክሽን ቡድን በቡታጅራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሲያካሄደው የነበረውን የኢንስፔክሽን ስራ በማጠናቀቅ የከተማው የፓርቲ ኮሚቴ በተገኙበት የማጠቃለያ ግብረ-መልስ ሰጥቷል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ አሰፋ ፈይሳ የኢንስፔክሽኑ ዋና አላማ ጠንካራ የኢንስፔክሸን ስራ በመስራት የፓርቲ አደረጃጀቶችን ያሉበት ሁኔታ ፈትሾ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት እንደሆነ ያስረዱ ሲሆን በዚህ መሰረት በፓርቲ ታቅደው የሚከናወኑ ተግባሮችን በስኬት ለመፈፀም የሚያስችል አደረጃጀት መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኃላፊው አቶ አሰፋ አክለውም እንዳሉት በኢንስፔክሽኑ ወቅት በከተማው ፓርቲ ፅ/ቤት በአብዛኛው በጠንካራ ጎን የሚገለፁ ለሌሎች መዋቅሮች ተሞክሮ ሊሆን የሚችል የፓርቲ አደረጃጀትና አስራር መኖሩን ማረጋገጥ መቻሉን ጠቅሰው ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ካሉ በኋላ በውስን ጉዳዮች በጉድለት የታዩትን ፈጥኖ እንዲታረሙ በማድረግ በቀጣይ ከዚህ ከፍ ላለ ስኬት መትጋት እንደሚገባ አመላክተዋል።
ሌሎች የዞኑ የኢንስፔክሽን ቡድኑ አባል አመራሮችም በከተማው የተሻለ የፓርቲ አሰራር መመልከታቸውን ገለፀው እነዚህን በዝርዝር የተሰጡ ግብረ-መልሶችን በመጠቀም የታየውን ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አቶ ሳሙኤል ማርቆስ የቡታጅራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው በዚህ ዙር የኢንስፔክሽን ቡድኑ የሰጣቸው ግብረመልሶች አስተማሪ መሆናቸውን ጠቅሰው በተሰጠን ግብረመልስ መሰረት ለተሻለ ውጤት በላቀ ትጋት ጠንካራ ፓርቲ በከተማው ለመገንባት ግብረ-መልሱን እንደ ግብዐት እንደሚጠቀሙበት ከገለፁ በኋላ የዞኑ የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን በየጊዜው ለሚያደርግላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።







በክልሉ በተያዘው በጀት አመት ብቻ 5 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ እንዲያገኙ እየተሰራ ነው :- አቶ ይግለጡ አብዛ
ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል "የጋራ ትርክት የበላይነት መጎናጸፍ፣ ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እና በሴቶች ኢኮኖሚ ተሳትፎ "ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ እንደገለጹት
በክልሉ በተያዘው በጀት አመት ብቻ 5 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ እንዲያገኙ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ በሁሉም ዘርፍ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት በማዘመን ረገድ የፋይዳ መታወቂያ የላቀ አበርክቶ እንዳለው አቶ ይግለጡ አብራርተዋል።
አንድ ሰው አንድ መታወቂያ እንዲኖረው ለማድረግ የተጀመረውን ግብ ለማሳካት ሴቶች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ኃላፊው ጠቁመዋል።
ሌብነት፣ዘረፋ፣ማጭበርበር እና መሰል ህገወጥ አሰራርን ለመከላከል የፋይዳ መታወቂያ ጉልህ ሚና እንዳለውም አቶ ይግለጡ ተናግረዋል።
በመሬት፣በንግድ ተቋማት፣በግብር ፣ በማዘጋጃ ቤቶች በሌሎች በልማትና በመልካም አስተዳደር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ተገቢ ስለመሆኑም ኃላፊው አስታውቀዋል።
የፋይዳ መታወቂያን በመጠቀም ዜጎች ያለ ምንም እንግልት ባሉበት ሆነው መንግስታዊ አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን ስርዓት መፍጠር ያስችላል ሲሉም አቶ ይግለጡ አብራርተዋል።
የፋይዳ መታወቂያ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋል የጊዜ፣የገንዘብ እና የጉልበት ብክነትን ከማስቀረት ባሻገር በአሰራር ላይ የሚያጋጥም አለመተማመን እና ጥርጣሬን ያስቀራል ብለዋል።
በመንግስታዊ አገልግሎት ላይ ግልጸኝነትን በመፍጠር እንዲሁም ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት ህብረተሰቡ የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም አቶ ይግለጡ አጽንኦት ሰጥተዋል።





"የጋራ ትርክት የበላይነት መጎናፀፍ ፣ለዘላቂ ሠላም ማረጋገጥ እና የሴቶች የኢኮኖሚ ተሳትፎ" ላይ ያቶከረ መድረክ የውይይት መድረክ ሆሳዕና ላይ ተጀምሯል።
ህዳር፣17/2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት "የጋራ ትርክት የበላይነት መጎናፀፍ ፣ለዘላቂ ሠላም ማረጋገጥ እና የሴቶች የኢኮኖሚ ተሳትፎ" በሚና መርህ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ሆሳዕና ከተማ መካሄድ ተጀምሯል።







"በዞኑ እንደሀገር የተያዘው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ኢኒሼቲቭ በአጠረ ጊዜ ለማሳካት በቁርጠኝነት እየተሰራ ይገኛል።"
አቶ ሙስጠፋ ሀሰን
(ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም)
በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ኢኒሼቲቭ ዕቅድ አካል የሆነ በ6.5 ሄክታር መሬት ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለመሸፈን የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በተገኙበት ዘር የመዝራት ስራ ተከናውኗል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን እንደዞን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ኢኒሼቲቭ በአጠረ ጊዜ ለማሳካት በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በባለፈው ዓመትም ከ50 ሄክታር መሬት በላይ ለዚህ ተግባር በሚሆን ሰብል መሸፈን መቻሉን አመላክተዋል።
በ2018 በጀት ዓመት ተግባሩን በተሻለ ለመፈፀም ዕቅድ ተይዞ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝና በዛሬ ዕለትም 6.5 ሄክታር መሬት በዘር የተሸፈነው ማሳ የዚህ አካል እንደሆነ አመላክተዋል ።
ዞኑ በግብርናው ዘርፍ በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ ከክልሉ ትልቅ አቅምና ዕቅድ ያለው እና ውጤታማ ዞን እንደሆነ ተናግረዋል ።
በቀጣይም የተያዘው ዕቅድ እንዲሳካ እያንዳንዱ በግብርና ዘርፍ የተሰማራ ፣ባለሙያ ፣አመራር እና አርሶ አደሮች ባላቸው ይዞታ ጥምር ግብርና በመተግበር በቤተሰብ ደረጃ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተጀመረው ስራ በሁሉም አካባቢዎች አስፍቶና አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሱ አበጋዝ እንደዞን 1 ሺህ 31 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር እንደተገባ እና እስከ አሁን 40% በላይ ማሳዎች በዘር የተሸፈነበት ሁኔታ እንዳለ ገልፀዋል ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለት ግብ ኢኒሼቲቭ አንዱ ምርትን በእጥፍ ማሳደግ መሆንኑ በመጥቀስ እንደዞን ዕቅዱን ለማሳካት የመደበኛና የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በማጠናከር ምርታማነታችን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለትም በዘር የተሸፈነው ማሳ የዚህ ተግባር አካል እንደሆነ አመላክተዋል ።
ከዚህ ጎን ለጎን በምግብ እህል እራስን መቻል ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ኢኒሼቲቭ ተግባር በዞኑ በትኩረት እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል ።
በዛሬው ዕለትም በቡኢ ከተማ አስተዳደር በቡኢ ዙሪያ ቀበሌ በዘር የተሸፈነው 6.5 ሄክታር መሬት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት አካል እንደሆጀ እና ተግባሩ ለማሳካት የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየመራው መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል ።
የሀገራችን ብልፅግና ለማረጋገጥ ግብርና ትልቁን ድርሻ ስለሚወስድ መላው የዞኑ አርሶ አደሮች እና የግብርና ባለሙያዎች በመደበኛ እና በበጋ መስኖ ስንዴ ተግባር የታየዘው ዕቅድ ተግባራዊ በማድረግ የበኩላቸው እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የመቂ ወንዝን ተከትሎ በሚገኙ አካባቢዎች 30 ሄክታር መሬት የበጋ መስኖ ስንዴ ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱና ዘር መዝራት መጀመሩን አስታውሰዋል ።
የሚመጡ አደጋዎች በራስ አቅም ለመቋቋም እንደከተማ አስተዳደር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የተጀመረው ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ በልዩ ትኩረት እየተተገበረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በዛሬው ዕለትም 6.5 ሄክታር መሬት በቡኢ ዙሪያ ቀበሌ ለዚህ ተግባር እንዲሆን በዘር የመሸፈን ስራ እንደተሰራ ተናግረዋል ።
በቀጣይም በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች ያልታረሱ መሬቶች በማረስ መኸር ከመግባቱ በፊት ታርሰው ምርት እንዲሰጡ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
የቡኢ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ፍቅሩ እንደከተማ አስተዳደር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የተያዘው ኢኒሼቲቭ ለማሳካት በበልግና በመኸር ወቅት ተግባሩ በመፈፀም ምርት አምርቶ የማከማቸት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ።
የከተማ አስተዳደሩ መንግስት ተግባሩ የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ።
ለዚህ ዓላማ እንዲውል በዛሬው ዕለት በዘር ለተሸፈነው ማሳ ለግብዓትና ለመካናይዜሽን የሚሆን በቂ በጀት በመመደብ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን በመግለፅ እንደተቋም በቀጣይ ከብቅለት በኃላ ያሉ ስራዎች ጠንካራ የክትትል ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሆነ ገልፀዋል ።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት አካላት በቀበሌው በማህበር የተደራጁ ወጣቶች በመደበኛ መስኖ እያለሙት የሚገኝ የአትክልት ልማት ስራ ጎብኝተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠለ ጫካ ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሠረት ሽፋ ፣የቡኢ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ አዳነ ጨምሮ የከተማው የፊት አመራር እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል በማለት የዘገበው የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው!!






















በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአርሶ አደሮች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ፤
#ቡታጅራ| ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአርሶ አደሮች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ የፌዴራል፣ የክልሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሄደ።
የንቅናቄ መድረኩ በኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በጋራ የተዘጋጀ ነው።
በንቅናቄ መድረኩ ማጠቃለያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ እንዳሳሰቡት የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባውን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ የተቀናጀ ርብርብ ያስፈልጋል።
ስራው የህዝባችንን የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት የሚያስችል፣የባለቤትነት ስሜትን የሚያረጋግጥ፣ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማረጋገጥ የሚያስችል ስለመሆኑም አቶ ይግለጡ አብራርተዋል።
ብክነትን መቀነስ፣ችግሮችን ተቀናጅቶ መፍታት፣ስራውን ስኬታማ ለማድረግ የተቀናጀ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።
በየደረጃው ትክክለኛ የፋይዳ ዲጅታል መረጃዎችን ማዘጋጀትና ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፣አርሶ አደሩንም በተለያዩ አደረጃጀቶች ተንቀሳቅሰን በአፋጣኝ እንዲመዘገብና ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ ስለመሆኑም አቶ ይግለጡ አብራርተዋል።
ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ትክክለኛና ህጋዊ ማንነትን የሚያረጋግጥ፣ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲኖር የሚያስችል፣በአገልግሎት ሰጪውና በተጠቃሚው መካከል ተአሚኒነትን የሚጨምርና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል፣ተጠያቂነትንና ግልጸኝነትን የሚያረጋግጥ መሆኑም ሃላፊው አስገንዝበዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ተወካይና የቢሮው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ሀቢብ በበኩላቸው የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ስራውን ለማሳካት ዋናው ጉዳይ ተገቢ ትኩረት መስጠት እንደሆነም አመላክተዋል።
የአርሶ አደሩን መረጃ ለማሰባሰብ የግብርና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸው ፣በስራው ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተቀራርቦ ለመፍታት ቢሮው በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም አሳውቀዋል።
ስራው የውዴታ ሳይሆን የግዴታ እንደሆነ ያነሱት አቶ አህመድ ፣በየደረጃው የሚገኙት አደረጃጀቶች ለስራው ስኬታማነት በተደራጀ አግባብ እንዲንቀሳቀሱም ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልሃፊዝ ሁሴን መድረኩ መግባባት የተፈጠረበትና ዕቅዱን ለማሳካት ቅንጅት የተፈጠረበት ነው ብለዋል።
በንቅናቄ መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ፣የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ተወካይና የቢሮው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ሀቢብ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣የግብርና ሚኒስቴር ተወካዮች፣የክልሉ የስራ ሃላፊዎች፣የዞንና የልዩ ወረዳ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።












በቡታጅራከተማ አስተዳደር ለተለያዩ የልማት ተነሺዎች ምትክ የሚሆን 10.536 ሄክታር መሬት ፀደቀ፤
#ቡታጅራ | ታህሳስ 15/2018
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በቡታጅራ ከተማ ለተለያዩ የልማት ተነሺዎች የሚሆን 10.536 ሄክታር መሬትና ለ40 የመንግስት ቤት ተከራዮች 6ሺ 950 ካሬ ሜትር መሬት አፅድቋል።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በከተማው ወስጥ ለተለያዩ የልማት ተነሺ ለሆኑ ለ82 ባለ ይዞታ አርሶ አደር እና 351 የአርሶአደር ልጆች ምትክ መሬት እና 40 የመንግስት ቤት ለሚለቁ ተከራዮች ተለወጭ የከተማ መሬት እንዲሰጣቸዉ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ካቢኔ እንዲፀድቅ ለክልሉ አስተዳደር እንዲቀርብ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አቅርቧል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የማኔጅመንት አካላት በቡታጅራ ከተማ የቀረበውን ዝርዝር መረጃና ተገቢነት በማጥራት ለዞኑ ካቢኔ እንዲፀድቅ ጠይቋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በዝርዝር የቀረቡለትን ማለትም ለ82 የመሬት ባለይዞታዎች 3.6 ሄክታርና ለ351ልጆቻቸው የሚሆን 6.866 ሄክታር በድምሩ 10 536 ሄክታር ምትክ የሚሆን መሬት ላይ በሠፊው ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ሌላው በከተማ አስተዳደሩ በተመሳሳይ ለልማት ለሚነሱ ለ40 የመንግስት ቤት ተከራዮች ምትክ እንዲሆን ያቀረበው 6ሺ 950 ካሬ ሜትር መሬት፤ የዞኑ ካቢኔ በዝርዝር ተመልክቶ በሙሉ ድምጽ ያፀደቀ ሲሆን ለክልሉ መንግስት የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚቀርብም ታውቋል በማለት የዘገበው የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።








በምስራቅ ጉራጌ ዞን "በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ቃል ለዞን ማዕከል የብልፅግና ፓርቲ አባላት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።
#ቡታጅራ| ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን "በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ቃል ለዞን ማዕከል የብልፅግና ፓርቲ አባላት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
አባላቱ በስልጠናው ማጠቃለያ በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት የተሰጠው ስልጠና የአባሉን አቅም የገነባናየአባሉን ተነሳሽነትና ቁርጠኝነትን ያሳደገ የብልፅግና ፓርቲ እሳቤን ወደ ታለመለት ግብ ለማድረስ ከፍተኛ ድርሻ የሚኖረው መሆኑን ገልፀዋል።
ምስራቅ ጉራጌ ዞን ከተመሰረተ ሁለት ዓመቱ ብቻ ቢሆንም በወሳኝ የልማት ዘርፎች ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ በላቀ ሁኔታ ዞኑን እና የዞኑ ተቋማትን የብልፅግና ተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አስተያየት ሰጭዎቹ በተለያዩ የልማት መስኮች የመፈፀም አቅምና የስራ ባህል ለውጥ የመጣበት መሆኑን ተናግረዋል።
በየደረጃው ያለው ፈፃሚ በችግር ያለመታሰር በሀገራዊ ህልሞች ላይ ትኩረት በማድረግ ተሞክሮዎችን በመቀመር ማስፋት ከአባላት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ባለሙያዎች በሁሉም ዘርፍ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የስራ አካባቢንና ስራን እንዲሁም እራስን በኃላፊነትና በተጠያቂነት መምራት፤ በሁሉም መስክ የሚታይ የስራ ባህል ለውጥ ማምጣት ላይ ትኩረት ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ ሰልጣኞቹ ተናግሯል።
"በመደመር መንግስት ዕይታ ፤ የዘርፎች እመርታ" ሥልጠና ማጠቃለያ የፓርቲያችን ፕረዚዳንት ዶ/ር ዐብይ አህመድ ያስቀመጡትን አቅጣጫ መነሻ ያደረገ ዋና ዋና ግቦችን የያዘ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።





















22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በወራቤ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል"ትውልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር " በሚል መሪ ሀሳብ 22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በወራቤ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣የክልሉ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ፣ከክልል፣ከዞኖች እና ከልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።











በምስራቅ ጉራጌ ዞን "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል ርዕስ ለዞን ማዕከል የብልፅግና ፓርቲ የአባላት ስልጠና መካሄድ ጀምሯል።
#ቡታጅራ| ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም
በብልፅግና ፓርቲ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ አባላት "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል ርዕስ ለዞን ማዕከል የብልፅግና ፓርቲ አባላት ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።
ስልጠናው "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።
ስልጠናው የአባሉን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም የሚገነቡ ልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚዳሰሱበት መሆኑ ተገልጿል።










"ትውልድ በስነ-ምግባር ተቋም በአሰራር" በሚል መሪ ቃል የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር የዓለም የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቀን እያከበረ ይገኛል።
ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም(ቡታጅራ)
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ በሀገራችን ለ21ኛ በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቀን "ትውልድን በስነ-ምግባር ተቋም በአሰራር" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት ቀኑን በየዓመቱ ስናከብር አስተውለን ቃላችንን አድሰን ተቋም በስነ ምግባር መምራት እንድንችል ነው ብለዋል።
መልካም የሆኑ ባህሎችን ማጉላት ያስፈልጋል ያለት አስተዳዳሪው ሙስናን ታግለን ሀገርን መገንባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
ሙስናን መታገል የእለት ተእለት ተግባራችን በማድረግ ሙስና ላይ የተሳተፉ አካላትን ማስተማር፤ ማረምና ማጋለጥ እንደሚገባ አስረድተዋል።
ትግሉን በማቀጣጠል ዞኑን ከሙስና ነፃ ማድረግ አለብን ያሉት አስተዳዳሪው ትውልድ ልማትን በማያደናቅፍ መልኩ በመቅረፅ የተሻለ ኢትዮጵያ መፍጠር ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ እንዳልካቸው ጌታቸው፤ የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሱ አበጋዝ፤ የዞኑ አጠቃላይ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።



"ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ የተከበረው 20ኛው የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ውጣታማ በሆነ መልኩ መከበሩ ተገለፀ።
#ቡታጅራ| ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር የ20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አፈጻጸም ግምገማ አካሄዷል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ የተከበረው 20ኛው የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ቅንጅትና መናበብ ተሞክሮ መሆን የሚችል በዓል መከበሩ ገልፀዋል።
ከቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጀምሮ የማህበረሰባችን እንግዳ ተቀባይነት በሚመጥን መልኩ ለማክበርና እንግዶችን ለመቀበል በትኩረት በተሰሩ ስራዎች ውጤታማ በዓል በማድረግ ማለፉን አንስተዋል።
እንደ ሀገር ስኬታማ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በማክበር ክልሉ አድናቆትን የተቸረውና ለሌሎችም ልምድና ተሞክሮ መሆን እንደቻለ አመላክተዋል።
ህዝብና አመራር በቅንጅት በመስራቱ በአሉ ስኬታማ እንደነበር ጠቅሰው በየደረጃው ድርሻቸው ለተወጡ ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ እንዳልካቸው ጌታቸው በበኩላቸው 20ኛ የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ደማቅና ስኬታማ በዓል ተከብሯል ብለዋል።
ዋና አፈ ጉባኤው የዞናል በዓል አከባበርና የእግዳ አቀባበል ሂደት አስመልክቶ የተፈፀሙ ዝርዝር ተግባራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት ዞኑ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መግቢያ በመሆኑ ዞኑን አቋርጠው ወደ ሆሳዕና ለሚያልፋ የ8 ክልል ልዑካን ቡድን በቡታጅራ ከተማ የዞኑ ማህበረሰብ በሚመጥን መልኩ እንግዶችን ተቀብለን መሸኘት ችለናል ብለዋል። ለዚህም አጠቃላይ የዞኑ ህዝብ፣ አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ፣ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የፀጥታ አካላትና የዞኑ የባህል ቡድን ላደረጉት አስተዋፆ ምስጋና አቅርበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሰለ ጫካ በዓሉ ህዝብና አመራር ከተቀናጀ ሁሉም ነገር ማሳካት እንደሚቻል ያሳየና ስኬታማ እንደነበር ገልፀዋል።
በዓሉ የማህበረሰብ አንድነትና አብሮነት እንዲሁም እንግዳ ተቀባይነት ማሳየት ያስቻለ ሁነት በማከናወን ውጤት የተገኘበት እንደነበረም አንስተዋል።
በቀጣይ በሁሉም መድረኮች አመራሩ በመናበብ መሰል መድረኮች ለማሳካት የነበሩ ጉድለቶችን በማረም መልካም ልምዶችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
በመድረኩም የዞኑ አስተባባሪዎች፣ የዞኑ ጠቅላላ አመራር፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በአጠቃላይ የበአል አከባበሩ ውጤታማ እንዲሆን ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ አስከ ፍፃሜው በቅንጅት የተሰራው ስራ ውጤታማ እንደነበረና ለቀጣይም ትምህርት የሚወሰድበት መሆኑን በመድረኩ አስተያየት የሰጡ ተሳታፊዎች ገልፀዋል ።


መግለጫ

በቡታጅራ ከተማ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን ገፅታ የቀየረ፣ ለነዋሪዎችና ጎብኚዎች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ እና ፕሮጀክት ጀምሮ የመጨረስ ብቃት የታየበት መሆኑን ሰልጣኞች ገለፁ
ህዳር 16/2018ዓ.ም
የብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ ሰልጣኝ አመራሮች በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ተገኝተው አስተያየታቸውን የሰጡን ሰልጣኞች እንደገለፁት የቡታጅራ ከተማ የኮሪደር ልማት የአመራርና የህዝቡ ቅንጅታዊ ስራ የታየበት እጅግ ውብና ማራኪ እንዲሁም ፕሮጀክት ጀምሮ የመጨረስ ብቃት የታየበት መሆኑን ገለፀዋል።
ስልጠናውና ጉብኝቱ ዕውቀትና ልምድ የተገኘበት ሁሉም በተሰማራበት መስክ በቁጭት ተነሳስቶ በላቀ ደረጃ በአካባቢው በመትጋት የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እንዲቻል ከፍተኛ መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው መረዳት ተችሏል።
መረጃው የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ ዘርፍ ነው






የም/ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የአቶ መሰለ ጫካ መልዕክትፓርቲያችን ብልጽግና በኢህአዴግ ዘመን የነበሩ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶችን እና አጋር በሚል ሲጠሩ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማካተት አቃፊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት የሚገነባ ‹‹ የብልጽግና ፓርቲ›› የሚሰኝ ኅብረ ሀገራዊ ፓርቲ ሆኖ የተቋቋመ ፓርቲ ነው፡፡ የፓርቲያችን ጥቅል ዓላማ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው፡፡ ብልጽግና ስንል ፈርጀ ብዙ ትርጓሜን አዝሎ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና ማኅበራዊ ገጽታ ያለው ነው፡፡
ኢኮኖሚ ብልጽግና ፣ የሕዝቦች መሠረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት የሚያስችል ፈጣን እና ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብ፣ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና የህዝቦችን ድህነትና ኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ መቻልን ያካተተ ነው፡፡
የፖለቲካ ብልጽግና ስንል ለዴሞክራሲ ባህል ማበብ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን በመገንባት፣ የሕዝቦች ነጻነትና እኩልነት ተረጋግጦ ሁሉም ኢትዮጵውያን ሰብአዊና ዴሞክሲያዊ መብቶቻቸው ተከብረውላቸው የሚኖሩባትን፣ ኅብረ ሀገራዊ አንድነቷ የተረጋገጠ፣ ፌደራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ጽኑ መሠረት ላይ ማቆም ነው፡፡
ማኅበራዊ ብልጽግና፤ መልካም ሀገራዊ ወጎችን፣ ዕሴቶችን እና ባህሎችን በማዳበር በሥነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራት፣ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ጤናማ ዜጋ መፍጠር፣ ከአስከፊ ማኅበራዊ ችግር የተጠበቀ ኅብረተሰብ መገንባት እና በሕዝቦች መካከል አዎንታዊ ሰላም በመፍጠር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡
ክልላችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና ዞናችን ምስራቅ ጉራጌ ዞን በ2015 ዓ/ም በመጨረሻው ነሐሴ ወር ላይ ተደራጅው ስራ የጀመሩ ቢሆንም ከተደራጁ ሁለት ዓመት እንኳን ሳይሞላ የክልሉን ብሎም የዞናችንን ህዝብ ተጠቃሚ ማድግ ያስቻሉ በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ማከናወን የተቻለበት እንዲሁም በቀጣይም በአጭር እና በረጅም ግዜ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የሀገራችን ኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ እተጋን እንገኛለን፡፡
ስለሆነም በዞናችን የምትገኙ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መላው የዞናችን ህዝቦች የፓርቲያችን የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ዕውን የማድረግ ራዕይ እንዲሳካ ለማስቻል የተመዘገቡ መልካም የልማት ውጤቶች በላቀ ደረጃ ቀጣይነታቸው እንዲረጋገጥና በትጋታችን የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ዕውን ለማድረግ ሁሉም በየተሰማራበት መስክ እንዲተጋና ለውጤት እንዲሰራ አደራ በማለት መልዕክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡



