በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ጳጉሜን 4 ''የማንሰራራት '' ቀን በቡታጅራ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።
#ቡታጅራ| ጳጉሜን 04/2017 ዓ/ም
‘ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሠራራት’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ያለው ጳጉሜን 4 የማንሠራራት ቀንን አስመልክቶ በክልሉ ኢንደስትሪ ክላስተር በቡታጅራ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዚህ ፕሮግራም ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንደስትሪ ክላስተር አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን አመሮችና ባለሙያዎች ፤ የማረቆ ልዩ ወረዳ አመራሮች ፣ የቡታጅራ የከተማና የመስቃን ወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በጠዋቱ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ማንሰራራትን የሚያበስሩ በቡታጅራ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ጉብኝት ተደርጓል።
የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በኢንዱስትሪ፤ በግብርና በቱሪዝምና በከተማ ልማት ዘርፍ በፈጠራና በፍጥነት ትጋትና ጥረትን በማሳደግ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን የተመላከተ ሲሆን ፕሮግራሙ በፓናል ውይይትና በሌሎች በተያዙ መርሀግብሮች የሚቀጥል ይሆናል።






ዜና ሹመት 16/12/2017
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የተሰጡ የተለያዩ ሹመቶች
1. ወ/ሮ ጀሚላ ጎሳ የም/ጉራጌ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ መምርያ ሀላፊ
2. አቶ ሰልማን ሳኒ የም/ጉራጌ ዞን ትምህርት መምርያ ሀላፊ
3.. ወ/ሮ ሙንተሀ ሽኩር - የዞኑ የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ
4. አቶ ደርቤ ታደሰ በካቢኔ ማዕረግ የዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ
5. አቶ መሀመድ ሳኒ - በካቢኔ ማዕረግ የግብርና መምሪያ ቡናና ቅመማቅመም ዘርፍ ኃላፊ
6. አቶ መሀመድ ሀሚድ የሚልሻ ጽ/ቤት ሀላፊ
7. አቶ ሻፊ ሽፋ - በፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ
8. ዶ/ር ሁሴን አልዬ - በግብርና መምሪያ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ሀላፉ
9. አቶ መልካም አበዛ - በግብርና መምሪያ ም / ሀላፊና አደጋና ስጋት መከላከል ፅ / ቤት ሀላፊ
10. አቶ ደለለኝ ሲዳ - በኢንተርፕራይዝና ስራዕድል ፈጠራ መምሪያ የከተማ ዘርፍ ስ/እድል ፈጠራ ሀላፊ
11. አቶ ሸምሱ አወል በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የመሬት ልማት ዘርፍ ሀላፊ
12. አቶ አሰግድ ታደሰ - በትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ
13. አቶ ሙህዲን ዳርሙሎ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የመንገድ ዘርፍ ሀላፊ
14. አቶ ታሪኩ በሬሳ- በውሃና ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ የመጠጥ ውሃ ዘርፍ ሀላፊ
15. ወ/ሮ ኤደን ከድር - በሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ፅ/ቤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ
ነሃሴ 08/12/2017 ዓ/ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ፅ/ቤት በ2017 በጀት አፈጻጸም ባስመዘገበው ውጤት በክልሉ አንደኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ።
ነሃሴ 08/12/2017 ዓ/ም
ፅ/ቤቱ በተጠናቀቀው በ2017 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የአፈፃፀም ውጤት በክልሉ አንደኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ በመሆን አጠናቋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ፅ/ቤት ኃለፊ ወ/ሮ ጀሚላ ጎሳ የተመዘገበው ወጤት አስመልክቶ ለመላው የዞኑ ማህበረሰብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት በዞኑ ጠንካራ የኢንስፔክሽን ስራዎች በመስራት በአጭር ጊዜ ውጤት እየተመዘገበ ነው ያሉት ኃላው በቀጣይም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም በየደረጃው የሚገኙ የፅ/ቤት አካላት የዞን፤የወረዳና የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዳነ ተሰማ በተመዘገበው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በቀጣይም ይበልጥ ኮምሽኑ ተጠናክሮ ስራዎች እንደሚሰራ ጠቁመዋል።




የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ''የፓርቲ ተቋም ግንባታ ለላቀ እምርታ'' በሚል መሪ ሀሳብ ለዞኑ ጠቅላላ
አመራር ስልጠና መስጠት ጀመረ!
ሐምሌ 08/2017 ዓ/ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ ቤት የፓርቲ_ተቋም_ግንባታ_ለላቀ_እምርታ በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት
ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ለዞኑ ጠቅላላ አመራር ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።
የስልጠናው ዋነኛ ዓላማም:ለስራ የተነሳሳ፣የሚመራውን ተቋም በብቃት የሚመራ
አመራር መፍጠርና የፓርቲ ውጤታማነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል
የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና እንደሆነም ተመላክቷል።
በአሁኑ ሰዓትም የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪና የዞኑ
የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ጫካ''መሰረታዊ የመሪነት ጥበብ እና
አገልጋይ አመራር'' በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ ላይ ስልጠናውን እየሰጡ ይገኛል።














